የምሥራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከናወነ ቆይቶ ዛሬ እሑድ ሰኔ 12 ቀን ይቋጫል፡፡ ደቡብ ሱዳን፣ ዑጋንዳና ሶማሊያን ጨምሮ ሌሎችም በፌስቲቫሉ ተሳትፈዋል፡፡ ከአገር ውስጥ የተለያዩ ክልሎች የባህል ቡድኖች ትርዒታቸውንም አቅርበዋል፡፡ ከውጭ የመጡት ልዑካን ብሔራዊ ሙዚየምና የኦሮሞ ባህል ማዕከልንም ጎብኝተዋል። ፎቶዎቹ የፌስቲቫሉን ልዩ ልዩ ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡