Thursday, September 21, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ የወርቅ መግዣ ዋጋን ወደ 35 በመቶ አሳደገ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ መግዣ ማበረታቻ ዋጋን ከነበረበት 29 በመቶ ወደ 35 በመቶ ከፍ አደረገ፡፡ ባንኩ ከዚህ በፊት ለወርቅ አቅራቢዎች ከዓለም አቀፍ የወርቅ ዋጋ ላይ 29 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ሊገዛ የነበረ ሲሆን፣ ከአሁን ጀምሮ ግን በ35 በመቶ ጭማሪ የሚረከብ ይሆናል፡፡

አዲሱ ጭማሪ የወርቅ አቅርቦትን የበለጠ ለማበረታታት የተደረገ ሲሆን ከ50 ግራም ጀምሮ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ የሚያቀርቡ በሙሉ ከጭማሪ ግዥ ዋጋው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሪፖርተር ከባንኩ ኃላፊዎች ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ወርቅ ያቀረቡ ብቻ ከተጨማሪ ዋጋው ተጠቃሚ ነበሩ፡፡

ባንኩ ከዓለም አቀፍ ዋጋ በላይ በሆነ ውድ ዋጋ ከወርቅ አቅራቢዎች የሚገዛው፣ በተለይ ባህላዊ ወርቅ አውጪዎች በትይዩ ገበያ ዋጋ (አንድ ዶላር ከ70 ብር በላይ) እንዲሸጡ የሚገደዱበትን ሁኔታ ለማስቀረት ሲሆን፣ ይህም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ውጤት እያስገኘ ነው፡፡ ምንም እንኳ ባንኩ በብር እየከሰረ ወርቅ ቢገዛም፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢው ግን ለአገሪቱ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ጭማሪ መግዣ ዋጋ (Premium) ማድረጉን ቀጥሏል፡፡

‹‹ማበረታቻው በሕጋዊ መንገድ ወጥቶ ወደ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ ደግፌ፣ በብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና የምጣኔ ሀብት ኃላፊ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በጥቁር ገበያ ምክንያት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የወርቅ ኤክስፖርት ገቢ ወደ 27 ሚሊዮን ዶላር አሽቆልቁሎ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በ2006 ደርሶበት ከነበረበት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛ ገቢ አንፃር ወርቅ ወደ ባንኩ መምጣት አቁሞ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በባለፉት ሁለት ዓመታት እየተሻሻለ መጥቶ የባንኩ መግዣ ዋጋ ከጥቁር ገበያ ጋር በመስተካከሉ፣ የወርቅ የውጭ ገቢ ወደ ነበረበት ተመልሷል፡፡ በባለፉት 11 ወራት ከወርቅ 513 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም ቡና ካስመዘገበው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ቀጥሎ ሁለተኛው ነው፡፡ አበባና ጫት 476 ሚሊዮን ዶላርና 372 ሚሊዮን ዶላር በተከታታይ አስገኝተዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጥቁር ገበያና በዋናው የምንዛሪ ተመን መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ከሄደ ወርቅ አሁንም በሕገወጥ መንገድ የመውጣቱ ዕድል ሰፊ ነው፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች