Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየሥዕል ቅርሶች አጠጋገን ሥልጠና ለማካሄድ የተደረሰው ስምምነት

  የሥዕል ቅርሶች አጠጋገን ሥልጠና ለማካሄድ የተደረሰው ስምምነት

  ቀን:

  የቋሚ የሥዕል ቅርሶች ጥገናና ክብካቤ ለማካሄድ የሚያስችል የሥልጠና መርሐ ግብር ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ማድረጉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ አርት ኮንሰርቬሽን ጋር በመተባበር የሚዘጋጀውና በቤልጂየም የሚደገፈው መርሐ ግብር የመግባቢያ ሰነድ ፊርማው የተፈጸመው ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው፡፡

   ባለሥልጣኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር)፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠናው መርሐ ግብር የቅርስ ጠባቂዎችንና ተንከባካቢዎችን ቁጥር የሚጨመርበትና በተቋሙ ብቻ ሳይወሰን በክልሎችም አቅም የምንገነባበትም ነው ብለዋል፡፡

  በኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ዘዴዎች ለሺሕ ዓመታት ጥንታዊና ባህላዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም የዘለቁ መሆናቸውን ያመለከቱት በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር ፍራንስዋ ዱማንት ናቸው፡፡

  አሁንም ድረስ የአገር ውስጥ ቅርሶችን ለማደስና ለመንከባከብ ውጤታማ መሆናቸው፣ ዘዴዎቹና ጥበቡ አሁንም በትውልዶች ውስጥ መኖሩን፣ አንዳንድ ቅርሶች ግን በጥሩ አጠባበቅና አያያዝ ዕጦት ምክንያት የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ያሉት አምባሳደሩ፣ ብቁ የጥበብና የቅርስ ጠባቂዎችን ለማፍራት እንዲሁም አቅም ለመገንባት በጥልቀት መሠራት እንዳለበትና የቤልጂየም መንግሥትም ይህን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡

  የመግባቢያ ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት ዋና ዳይሬክተሩና አምባሳደሩ ናቸው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...

  መኖሪያ ሸጦ መዞሪያ!

  እነሆ ከመካኒሳ ወደ ጀሞ ልንጓዝ ነው። ቀና ሲሉት እየጎበጠ...

  በምግብ ራሳችንን የመቻል ፈተና

  በጋሹ ሃብቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በምግብ ራሳችንን መቻል እጅግ በጣም የተወሳሰበ...