Thursday, February 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አገሮች በኮንጎ ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አገሮች በኮንጎ ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ

ቀን:

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መቆም ያልቻለውና በየጊዜው የሚያገረሸው የኢኮኖሚ ጦርነት በርካታ የአገሪቱ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉና የጎረቤት አገሮች ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ እንዲሞቱ፣ አካል ጉዳተኛ እንዲሆኑና ቤት ንብረታቸው እንዲወድምም አድርጓል፡፡ በተለይ ሴቶችና ሕፃናት የሞት፣ የመደፈርና የስደት ሰለባ ሆነዋል፡፡

ሰሞኑን በምሥራቅ የአገሪቱ ክፍል ያገረሸው ጦርነት ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አገሮች ለመፍትሔው ጣልቃ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል ለተከሰተው ግጭት ኮንጎ ሩዋንዳን መወንጀሏና ‹‹ሩዋንዳ የቱትሲ አማፅያንን ትደግፋለች›› ማለቷን ሩዋንዳ ብታጣጥልም፣ ኮንጎ ለተገደሉባት ወታደሮችና በአካባቢው ለፈጠረው መፈናቀል ሩዋንዳን ኮንናለች፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በማዕድን ሀብቷ የምትታወቀው ኮንጎ፣ ከኤም23 ሙቭመንት አማፅያን በተጨማሪ በርካታ ታጣቂ ኃይሎች ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ የሚዋጉባት ናት፡፡

በኤም23 ታጣቂዎችና በኮንጎ ወታደሮች መካከል ሰሞኑን ያገረሸውን ጦርነት ለማስቆምም ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በኬንያ የተቀመጡት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል አገሮች መሪዎች፣ በኮንጎ በቅርቡ ያገረሸውን ጦርነት ማስቆም በሚቻልበት ላይ መክረዋል፡፡

በኤም23 ታጣቂዎችና በኮንጎ ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ለማስቆምም በኮንጎ የአባላቱን ጥምር ጦር ለማስፈር ከስምምነትም ተደርሷል፡፡

ኤም23 ለዓመታት ያህል ከኮንጎ ወታደሮች ጋር የሚዋጋው የወርቅና የፕላቲኒየም ማዕድን ክምችት ያለበትን የኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል ለመቆጣጠር ነው፡፡ ከሩዋንዳና ኡጋንዳ የሚመጡ ታጣቂዎችም በዚሁ ጦርነት ይሳተፋሉ፡፡

ይህ መሆኑ ደግሞ ብሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ታንዛኒያን፣ ኡጋንዳንና ኮንጎን በአባልነት የያዘው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል አገሮች ጥምር ኃይል በቦታው ሲሰማራ ችግር ሊገጥመው ይችላል የሚል ሥጋት አጭሯል፡፡

ቪኦዴ በፖሌ ኢንስቲትዩት የግጭትና ግጭት አፈታት ተመራማሪና የኮንጎ መላ አፈላላጊ ጆኤል ባራካን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የኮንጎ መንግሥት የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሐሳብ በቀጣናው የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጥሩ መንገድ ይሉታል፡፡

በጦርነቱ የኤም23 ታጣቂዎች ይዋጋሉ ይባል እንጂ፣ ሩዋንዳና ኡጋንዳ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉበት መሆኑ፣ እነሱ አባል በሆኑበት በምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ችግሩን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ሊያከሽፍ ይችላል ይላሉ፡፡

የፖለቲካ ተንታኝና ተመራማሪ ኒታንዮማ ሩኩምቡዚ እንደሚሉት፣ የኮንጎ ወታደሮች ብቻቸውን በአገሪቱ ያለውን ጦርነት ሊያስቆሙ አይችሉም፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወይም በአፍሪካ ኅብረት ሥር ሆኖ ከተደራጀ በተሻለ ደረጃ ግጭቱን ማስቆም ይቻላል፡፡

የቀጣናው አባል አገሮች አሁን ላይ ያቀዱት በሰሜን ኪቩ፣ በደቡብ ኪቩና በኢቱሪ ግዛቶች ወታደሮች ለማሰማራት ነው፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል አገር መሪዎች ወታደሮቻቸውን በኮንጎ ለማሰማራት ከውሳኔ ቢደርሱም፣ ኮንጎዎች በግዛታቸው በተለይ ለጦርነቱ ድጋፍ ያደርጋሉ የሚሏቸውን የሩዋንዳንና ኡጋንዳን ወታደሮች እንዲገቡ ይፈቅዳሉ ብሎ መቀበል አይቻልም፡፡

‹‹ሕዝቡ የቀጣናውን ወታደሮች የሚቀበል አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የዚህ ኃይል ተቀናቃኞች በፓርላማና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አሉ፡፡ የሩዋንዳንና የኡጋንዳን ወታደሮች ጣልቃ ገብነት አይደግፉም፤›› ሲሉም ባራክ ተናግረዋል፡፡

የኢኮኖሚ ተደርጎ በሚወሰደውና ኮንጎን ለዓመታት የደም ምድር ባደረገው ጦርነት፣ ባለፉት አምስት ቀናት ብቻ ከምሥራቅ ኮንጎ 25 ቪሕ ሕዝቦች ከቤታቸው ተሰደዋል፡፡ አምስት ሺሕ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች ባደረጉት ስምምነት መሠረት፣ በኮንጎ ሰላም ለማስፈን ጦራቸው ከኮንጎ ጦር ጋር ተጣምሮ የሚሠራ ሲሆን፣ በምሥራቅ ኮንጎ የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲያባራም ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...