Wednesday, September 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በቢሾፍቱ ሐይቅ ዳርቻ ከ750 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው ሆቴልና ሪዞርት ሥራ ሊጀምር ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ቲኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቢሾፍቱ ሐይቅ ዳርቻ ከ750 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴልና ሪዞርት የፊታችን ቅዳሜ እንደሚያስመርቅ  አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሆን፣ ሆቴልና ሪዞርቱ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የቲኬ ሆቴልና ሪዞርት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታሪኩ ተስፋዬ እንደገለጹት፣  ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚመረቀው ሆቴልና ሪዞርት፣ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ በርካታ ዜጎች በሆቴሉ ግንባታ ወቅትም በርካታ ሰዎች የሥራ ዕድሎችን ማስገኘቱን የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

 ሆቴሉ ከ78 በላይ ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎች ያሉት መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሆቴልና ሪዞርቱን አስገንብቶ ለማጠናቀቅ 13 ዓመታት መፍጀቱንና ከፍተኛ ወጪ መጠየቁን አስረድተዋል፡፡

ሆቴልና ሪዞርቱም በአጠቃላይ በ2,917 ካሬ ሜትር ላይ ማረፉን ጠቁመው፣ በተለይም ከተማው አብዛኛውን ጊዜ የአገር ውስጥም ሆኑ የውጭ አገር ቱሪስቶች በብቃት የሚያስተናግዱ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ታሪኩ፣ ከዚህም በተጨማሪ ዘመናዊነት የተላበሱ የመዝናኛ ቦታዎችንም ጭምር ያካተተ እንደሆነም አክለዋል፡፡

ሆቴሉ የሚጠቀምባቸው ፈሳሽ ቆሻሻዎችን በማጣራት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ደግሞ ለአገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሆቴሉ ላይ የሥራ ዕድል የሚያገኙት የከተማው ነዋሪዎች እንደሆኑ ገልጸው፣ ይኼም በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለውን የሥራ አጥነት ቁጥር በተወሰነ መልኩ ሊቀርፍ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ሆቴልና ሪዞርቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ በርካታ ተግዳሮቶች እንደገጠማቸው የሚናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ አሁን ባለው የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚስተዋለው ለግንባታ የሚሆኑ ግብዓቶች መወደድ ሆቴሉን በታለመው ጊዜ እንዳይጠናቀቅ አድርጎታል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች