Sunday, September 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የደረጃዎች ኤጀንሲ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ባለመገኘታቸው ሊሰጥ የነበረውን መግለጫ ሰረዘ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የኅብረተሰቡን ችግር ይቀርፋሉ የተባሉ ደረጃዎችን በተመለከተ ማክሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በተቋሙ አዲሱ ሕንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሊሰጥ የነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የተወሰኑ ሚዲያዎች የተገኙ ቢሆንም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ባለመገኘታቸው መግለጫ መስጠቱን ሰረዘ፡፡

በኤጀንሲው የተሰረዘው መግለጫ ትኩረቱን ያደረገው በምግብና እርሻ፣ በአካባቢና ጤና፣ በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች፣ በኤሌክትሮ ኬሚካል፣ በኮንስትራክሽን፣ እንዲሁም በሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፎች የተዘጋጁ ደረጃዎች ላይ ማብራሪያ ለመስጠት የተዘጋጀ ነበር፡፡  

ከባለድርሻ አካለት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የምርትና የአገልግሎት ደረጃዎች በብሔራዊ ምክር ቤት መፅደቁንና ስለደረጃዎቹ በተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫና ማብራሪያ ሊሰጥ እንደነበር ለሪፖርተር ጋዜጣ የተላከው የጥሪ ወረቀት ያሳያል፡፡

የኅትመት ሚዲያና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ ያለ ካሜራ በተቋሙ በመገኘታቸው መግለጫውን ለሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. መተላለፉን የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ይስማ ጅሩ ተናግረዋል፡፡

አቶ ይስማ ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመስጠት የኅትመት፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን በአጠቃላይ ሦስት ሚዲያዎች መገኘት አለባቸው ብለዋል፡፡

በመሆኑም የተገኙት ሚዲያዎች በቂ ባለመሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡

በተደጋጋሚ በመንግሥት ተቋማት የሚጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ካልተገኙ ሲሰረዙ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች