Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃንን የመንግሥትና የግል ቀጣሪዎች እንደማይቀጥሯቸው ተገለጸ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃንን የመንግሥትና የግል ቀጣሪዎች እንደማይቀጥሯቸው ተገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማኅበር፣ ከግል ከፍተኛ ተቋማት የሚወጡ ምሩቃን በአንዳንድ የመንግሥትና የግል ቀጣሪዎች ተቀባይነት እንዳላገኙ አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ ይህንን ያስታወቀው ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ውይይት ነው፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሞላ ፀጋዬ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ አንዳንድ የመንግሥትና የግል ቀጣሪዎች ከግል ከፍተኛ ተቋማት የሚወጡ ተማሪዎችን አይቀጥሩም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለያዩ የትምህርት መርሐ ግብሮች ተመርቀው በሥራ ላይ የሚገኙ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የወጡ ሠራተኞችም፣ ‹‹የደረጃ ዕድገት አንሰጥም›› እንደተባሉም አስረድተዋል፡፡

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን አንቀጥርም የሚሉ የመንግሥትና የግል ድርጅቶች መኖራቸውን፣ ከእነዚህም መካከል ባንኮችና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችም መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

ከመንግሥት ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ መሆኑን፣ ሌሎችም የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ምሩቃንን አንቀበልም (አንቀጥርም) መባላቸውን ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

በተለይ በአንዳንድ የክልል ከተሞች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ተመርቀው በሥራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች፣ የደረጃ ዕድገት እንደማያገኙና የማይቀጥሩ ተቋማት እንዳምሉ ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎችን ከማይቀበሉና ለሠራተኞችም የደረጃ ዕድገት ከሚከለክሉ ክልሎች መካከል አማራና ደቡብ ይገኙበታል ብለዋል፡፡

የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፣ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የተደረገው ውይይት፣ የመጀመርያ መሆኑንና የውይይት መድረኩ በቀጣይ መከናወን የሚገባውን ለማወቅ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚወጡ ተመራቂዎችን የግልና የመንግሥት ቀጣሪ መሥሪያ ቤቶች አንቀጥርም የማለት መብት እንደሌላቸውም ገልጸዋል፡፡

ቀጣሪዎች ትኩረት ሊያደርጉ የሚገባቸው በመሥፈርታቸውና በብቃት የሚያልፉት ላይ መሆኑን የገለጹት ነገሪ (ዶ/ር)፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ከዚህ በዘለለ ጭፍን ጥላቻ ማሳየት ወንጀል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡  

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመጡ ተማሪዎች ብቃት እንደሌላቸው፣ ከመንግሥት ትምህርት ተቋማት የሚመጡት ደግሞ ብቃት እንዳላቸው ማሰብ ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ለማለትም በመጀመርያ መፈተሽና ማጣራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡ ችግሩንም በዘላቂነት ለመፍታት ከትምህርት ሚኒቴስርና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመሆን ጉዳዩን እንደሚያዩት የገለጹት ሰብሳቢው፣ በጥናት ላይ የተመሠረተ ማስተካከያ ማድረግ ተገቢ መሆኑንና ቋሚ ኮሚቴውም የድርሻውን እንደሚወጣ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...