Sunday, April 14, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ መኖሪያ ቤታቸው ገብተው ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው]

 • እንዲያው የዚህ አገር ሁኔታ እያሳሰበኝ ነው፡፡
 • አታስቢ… መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል።
 • እሱ እኮ ነው የሚያሳስበኝ፡፡
 • የቱ?
 • መጪው ጊዜ፡፡ 
 • እመኚኝ አሁን ያለው ጨለማ ይገፈፋል፣ አታስቢ ስልሽ፡፡
 • ሰላማዊ ዜጎች በየአካባቢው እየተገደሉ፣ እርስ በርስ መጠፋፋታችን እየቀጠለ እንዴት ብሎ ጨለማው ይገፋል? 
 • እመኚኝ ስልሽ? 
 • ምኑን ልመንህ?
 • ይህ ጊዜ ማለፉ አይቀርም። 
 • ጊዜውማ ማለፉ የት ይቀራል? 
 • እሱን እኮ ነው የምልሽ፣ ያልፋል፡፡
 • መከራችን መቼ አለፈ? ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት አይደለም እንዴ? 
 • ቢሆንም አብሮነታችን ይመለሳል፣ ያኔ ሰላም ይመጣል።
 • እንደ አፍህ ቢሆንማ ጥሩ ነበር። 
 • እመኚኝ ስልሽ?
 • እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ? 
 • ጥሩ ጠይቂኝ፡፡
 • አሳምነኝ፡፡
 • ምን አልሽ? 
 • እመኚኝ ከምትለኝ…
 • እ…?
 • ዕድሉን ልስጥህ አሳምነኝ፡፡
 • ሰላም ይሆናል እመኚኝ፡፡
 • አሁን አምኛለሁ። 
 • ምን? 
 • ከዚህ ሌላ የምትለው እንደሌለህ።
 • እንዴት እንደዚያ ትያለሽ? ትክክል አይደለሽም፡፡
 • እምነኝ ስልህ?
 • ምኑን?
 • አንተም አታምንበትም። 
 • እንዴት?
 • እመነኝ ስልህ? 

[ክቡር ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪያቸውን አስጠርተው መረጃ እንዲያቀርብላቸው እየጠየቁ ነው]

 • በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተፈጠረ ስለተባለው ጉዳይ መረጃ እፈልጋለሁ፣ ምንድነው የሆነው?
 • የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ናቸው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንደሚባለው ወረራ ፈጽመዋል? 
 • ወረራ እንኳን አይደለም ክቡር ሚኒስትር። 
 • እና ምንድነው የተከሰተው? 
 • በክልሉ የሚገኝ ሰፊ የወርቅ ማውጫ ነው የተቆጣጠሩት። 
 • እና ይህ ወረራ አይደለም? 
 • ወረራ አይደለም ያልኩትበት ምክንያት ታጣቂዎቹ በዚህ አካባቢ ከሠፈሩ በርካታ ዓመታት ስለተቆጠሩ ነው። 
 • በርካታ ዓመታት?
 • አዎ፣ ኑሯቸውን በዚህ አካባቢ ካደረጉ ከስምንት ዓመት በላይ ተቆጥሯል። 
 • እንዴት? 
 • ቀደም ሲል የነበረው መንግሥት በአካባቢው እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸው ነው። 
 • እንዴት? ለምን? 
 • በደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ጥል የተለያዩ መንግሥታት ይደግፉ ነበር።
 • እና?
 • በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥትም ተመሳሳይ ድጋፍ ያደርግ ነበር። 
 • ታዲያ እኛ የምንደግፈው ታጣቂ የለም? ለምን እስካሁን ለቀው አልወጡም?
 • ጥያቄው እሱ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት? 
 • ከድንበራቸው አልፈው 150 ኪሎ ሜትር ወደ እኛ ወሰን መዝለቃቸው ብቻ ሳይሆን፣ የፀጥታ መዋቅራችን እንቅስቃሴያቸውን ይከታተል ነበር ለማለት ያስቸግራል። 
 • እንዴት ሊሆን ይችላል? 
 • ጥያቄው ይኼ ብቻ አይደለም ክበር ሚኒስትር፡፡
 • እ… ሌላ ምን አለ?
 • ነፍጥ ያነሳብን የውስጣችን ታጣቂ ቡድን ላይ ጠንካራ ዘመቻ ስንጀምር የሸሸው ወደ ጋምቤላና ወደ እዚህ አካባቢ ነው። 
 • ግንኙነት አላቸው እያልከኝ ነው? 
 • ለጊዜው ያረጋገጥነው ነገር የለም፣ ነገር ግን…
 • ግን ምን?
 • ከፍተኛ የጦር መሣሪያ ወደ አገር ውስጥ እየገባ ያለው በዚህ አካባቢ ነው። 
 • እህ…
 • ይኼ ክቡር ሚኒስትር…
 • እ… እየሰማሁ ነው… ቀጥል…
 • ዋነኞቹ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች የወርቅ ጣቢያውን የተቆጣጠሩት ታጣቂዎች ናቸው። 
 • እህ… አሁን ነገሩ ግልጽ እየሆነልኝ ነው። 
 • ምን ተገለጸልዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ይህ ቡድን በኢትዮጵያ ግዛት የከረመው ውኃና ግጦሽ ፍለጋ አለመሆኑ ነዋ፡፡
 • እንደዚያ አለመሆኑ ግልጽ ነው። 
 • ተጨማሪ ምርመራ መደረግ አለበት። 
 • እያደረግን ነው፣ በተለይ የግብፅ እጅ ሊኖር እንደሚችል ምልክቶች አሉ ክቡር ሚኒስትር።
 • የጀመራችሁትን ቀጥሉ፣ ነገር ግን ተጨማሪ ምርመራ መደረግ አለበት።
 • ምን ዓይነት ምርመራ ነው?
 • ሰፋ ያለ ምርመራ መደረግ አለበት፣ በተለይ…
 • እየሰማሁ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በተለይ ጁንታው ሥልጣን ላይ እያለም ሆነ ከለቀቀ በኋላ የነበረው ግንኙነት በጥልቀት ይፈተሽ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በግጭት ለተጎዱ ልጆች 80 ሺሕ መጻሕፍት ማሠራጨት መጀመሩን ኢትዮጵያ ሪድስ አስታወቀ

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ከትምህርት ቤት ለተስተጓጐሉ፣ በሥነ ልቦናና በሌሎች...

የም እና መስህቦቿ

በቱባ ሀገሬ የም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ239...

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

አንዴ? ምን አገኘሽ? ምን አገኘሽ ማለት? ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው? እ... ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው። እንዴት? ምንድነው ነገሩ? በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ? አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር...