የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመፍታት በቀጣይ አምስት ዓመታት መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት የተናገሩት፡፡ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ሲተገበር የነበረው የትምህርት ሥርዓት፣ የትምህርት ተቋማትን በማስፋፋት ላይ እንጂ ጠንካራ ዜጋን ማፍራት በሚችሉ ምሁራንና የትምህርት ግብዓቶችን ማሟላት ላይ ያተኮረ አለመሆኑ ለትምህርት ጥራቱ ውድቀት ምክንያት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል። እየተስተዋለ ያለው የትምህርት ጥራት ስብራትና ውድቀት ለአገር ውድቀት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ያመለከቱት ሚኒስትሩ፣ ለዚህም ምክንያት ናቸው የተባሉ ጉዳዮችን የመለየት ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡