Thursday, December 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊ‹‹በኮቪድ ተይዘው የሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው›› የጤና ሚኒስቴር

  ‹‹በኮቪድ ተይዘው የሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው›› የጤና ሚኒስቴር

  ቀን:

  ‹‹በአሁኑ ጊዜ፣ በኮቪድ ተይዘው የሆስፒታል ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር፣ እየጨመረ ሲሄድ እያየን ነው፡፡ የሕመሙ ተጠቂዎች፣ በአብዛኛው ክትባት ያልወሰዱ ናቸው፤›› በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያሠፈሩት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ናቸው፡፡

  የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ አሁንም ብዙዎችን እየጎዳ መሆኑን፣ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር፣ ክትባቱን መውሰድ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን፣ የተከተቡ ሰዎች በሽታውን ለመቋቋም የተሻለ አቅም እንዳላቸው፣ በጽኑ ለመታመምም ሆነ በበሽታው ለመሞት ያላቸው ዕድል ዝቅተኛ መሆኑንም አመልተዋል፡፡

  በኢትዮጵያ፣ እስካሁን 42.5 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት የወሰዱ ቢሆንም፣ 342,108 ሰዎች ብቻ ከስድስት ወር በኋላ የሚሰጠውን የማጠናከሪያ ክትባት መውሰዳቸውን ያስታወቀው የጤና ሚኒስቴር፣ ተደራሽነቱን ለማሻሻል ሌላ ዙር የኮቪድ 19 የክትባት ዘመቻ መጀመሩን ገልጿል፡፡

  በዕለታዊው የኮቪድ-19 መረጃው እንደሚያሳየው፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ (ከሰኔ 14 ቀን-20፣2014 ዓ.ም.) ስምንት ሞት ሲመዘገብ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ቁጥር 3147 ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 487,683 ሲደርስ፣ እስካሁን ድረስ 459,714 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ታውቋል፡፡

  የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል 3ኛው ዙር የመከላከያ ክትባት በአዲስ አበባ ከሰኔ 13 ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ሁሉ በመንግሥት ጤና ጣቢያዎችና በተመረጡ ጊዜያዊ መስጫዎች በዘመቻ መልክ እየተሰጠ ነው፡፡ የከተማዪቱ የጤና ቢሮ እንዳስታወቀው፣ በዚህ የክትባት ዘመቻ ከ240 ሺሕ በላይ የክትባት ዶዝ ለመስጠት ታቅዷል፡፡

  ክትባቱን ኅብረተሰቡ በአግባቡ በመውሰድ ራሱን የኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትለው ሕመምና ሞት እንዲጠበቅና በመከላከል ሒደቱ የበኩሉን እንዲወጣም አሳስቧል፡፡

  ለክትባት ዘመቻው ስኬት እንዲረዳም ቢሮው የክትባት አሰጣጡን በተመለከተ ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱን ገልጿል፡፡

  የጤና ሚኒስትሯ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሁሉ፣ ክትባቱን እንዲወስዱ እንዲሁም ክትባት ከወሰዱ ስድስት ወር ያለፋቸው፣ የማጠናከሪያ (ቡስተር) ክትባት በመውሰድ ራሳቸውን እና ማኅበረሰቡን እንዲከላከሉ አሳስበዋል።

  በተያያዘ ዜና የጤና ሚኒስቴር ሰሞኑን ከቻይና መንግሥት 10 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባትን መረከቡን አስታውቋል፡፡

  ቻይና ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ቃል ገብታው ከነበረው የ20 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ውስጥ 10 ሚሊዮኑን የቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ዛኦ ዚያን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

  አምባሳደር ዛኢ ዚያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቀደም ሲል አራት ሚሊየን ዶዝ ክትባት መንግሥታቸው ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...