የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አንስቷል፡፡ ከትናንት በስቲያ፣ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በባህር ዳር ስታዲየም ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ባደረገው ግጥሚያ 4ለ0 በመርታቱ ነው፣ የቅርብ ተፎካካሪውን ያምናውን ሻምፒዮን ፋሲል ከነማን በአራት ነጥብ በልጦ ባለድል የሆነው፡፡ ፈረሰኞቹ ለ15ኛ ጊዜ ድሉን ካጣጣሙ በኋላ ደስታቸውን ከደጋፊያቸው ጋር በስታዲየሙ ገልጸዋል፡፡