Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየጣሊያንን ፕሬዚዳንታዊ ሽልማትን የተቀዳጀው ዕውቁ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ

የጣሊያንን ፕሬዚዳንታዊ ሽልማትን የተቀዳጀው ዕውቁ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ

ቀን:

ፒያኖ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃዊ ቅርስ ባይሆንም የሙዚቃን አዲስ ገጽታ በማሳየት በኩል የቅርብ ዘመናት ትውልድ ሙዚቀኞችን መሳቡ አልቀረም፡፡ ከእነዚህም መካከል ከአገሩም አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፒያኖ ረቂቅ ሙዚቃ ተጫዋችነቱ ግርማ ይፍራሸዋ ይጠቀሳል፡፡

ከእርሱ በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአምስት አሠርታት በላይ ዝናቸው የናኘው መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም (እስራኤል) ያደረጉት የ99 ዓመቷ የዕድሜ ባለፀጋ እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ግርማ የርሳቸውን ፈለግ በመከተል በተለያዩ አገሮች ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ከአውሮፓ እስከ አውስትራሊያ የፒያኖ ኮንሰርቱን አቅርቧል፡፡ ብሉይ (ክላሲካል) ሙዚቃን ከኢትዮጵያ ትውፊት/አላባ ጋር በማስተሳሰር የራሱን ቱባ ሙዚቃ በመሥራትና በመቀመርም ይጠቀሳል፡፡

ሙዚቀኛ ግርማ በፒያኖ ረቂቅ ሙዚቃ ሙያው ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋጽኦ የጣሊያን መንግሥት ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ዘንድ ትልቅ ክብር ያለውን ፕሬዚዳንታዊ ሽልማትን ተሸልሟል፡፡

የጣሊያንን ፕሬዚዳንታዊ ሽልማትን የተቀዳጀው ዕውቁ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ሽልማቱን አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ከአምባሳደሩ እጅ ተቀብሏል፡፡ ኤምባሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ ‹‹ኤ ግራንድ ፕሬዚዳንሻል አዋርድ-ዘ ኦርደር ኦቭ ዘስታር ኦቭ ኢታሊ›› የተሰኘውን ፕሬዚዳንታዊ ሽልማትን ለማስተር ፒያኒስት ግርማ ያበረከቱት የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ ናቸው፡፡

የፒያኖው ጌታ ግርማ ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ባሰማው ዲስኩር ‹‹ለሙዚቃ የከፈልኩትን የፍቅር ዋጋ [ሽልማቱ] ከፍሎልኛል ብዬ አስባለሁ፤›› ብሏል፡፡

የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን ለማክበር የተገኙት የአርጤመስ የዳንስ ቡድን አባላት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በሚገኘው ቪላ ኢታሊያ ውስጥ ትርዒታቸውን አሳይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ተወልዶ ያደገው ሙዚቀኛው የፒያኖ ጌታ ግርማ ይፍራሸዋ በገጸ ታሪኩ እንደተመለከተው፣ የሙዚቃ ሕይወቱን አሐዱ ብሎ የጀመረው ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ የሆነውን ክራር በመጫወት ነው፡፡

በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ሲማር በኋላ ላይ ለተጠበበበት ለብሉይ ሙዚቃ (ክላሲካል) ተጫዋችነት ካበቃበት ፒያኖ ጋር ተዋውቋል፡፡ ከፍተኛ ትምህርቱን በቡልጋሪያ ሶፊያ ስቴት ኮንሰርቫቶሪ ኦቭ ሙዚቃ በመከታተል ተመርቋል፡፡ በተከታታይም በለንደን የሮያል ሙዚቃ አካዴሚና በላይፕዚንግ የሙዚቃና ቴአትር ተቋም ብሉይ ሙዚቃን ለመቅሰም ችሏል፡፡

በቡልጋሪያ የታላላቅ ሙዚቀኞችን የነሞዛርት፣ ቤቶቨን፣ ሹማን፣ ሹበርት፣ ቾፒንና ዴቡሲ ሥራዎች በማቅረብም አድናቆትን አትርፏል፡፡

በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ፒያኖን ያስተማረው ግርማ፣ አገራዊ ሙዚቃንና ብሉይ ሙዚቃን አስተሳስሮ፣ ብሂልን ከባህል አዛምዶ በአገር ውስጥ በውጭ አገሮች ሥራዎቹን አቅርቧል፡፡

ካሳተማቸው የክላሲካል (ብሉይ) ሙዚቃ አልበሞቹ መካከል ‹‹ሼፈርድ ዊዝ ዘ ፍሉት›› (ባለዋሽንቱ ዕረኛ)፣ ‹‹ላቭ ኤንድ ፒስ›› (ፍቅርና ሰላም)፣ መለያ ቀለሜ (ከሚካኤል በላይነህ ጋር)፣ ሰመመን፣ እልልታ ይገኙበታል፡፡

የታዋቂውን ገጣሚና ሠዓሊ ገብረክርስቶስ ደስታ ‹‹ሀገሬ›› ግጥምን በፒያኖ አቀናብሮ በማቅረቡም አድናቆትን ማትረፉ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...