Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የፈስ አፈርሳታ

ትኩስ ፅሁፎች

ፈስን የዓይነ ምድር ወላፈን ይሉታል አለቃ ደስታ ተክለወልድ በዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላታቸው፡፡ እንዲያውም በመላ ፈስ ዳለቻ ነው ሲሉም ያክሉበታል፡፡ በፈስ ላይ የተመሠረተ ሥነ ቃልንም  ‹‹የጠበኛ ፈስ ዓይን ያፈስ›› ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡  ሌሎች ከፈስ ጋር የተያያዙ ፈትሎችን እንደሚከተለው አስፍረዋል፡፡

ፈሰ ከንቱ (ቲ) የፈሱ ሽታ ራስ የሚበጠብጥ ሆድ የሚቆርጥ የሚያም ቁናሳም፡፡ ፈሳም፡፡ ፈረሱን ጠበሰ፣ ሮጠ ሸሸ ጋለበ (የአሮጊት ፈስ) ክረምት አፈራሽ ነገር፣ በበጋ እንደ ፈስ የሚበን የሚተን፣ ክብ እንክብል ዓይን የሚያኽል ፍጥረት፡፡

ልጆች በተሰበሰቡበት ፈስ ተፈስቶ የፈሳው ባይታወቅ፣ የፈስ አፈርሳታ ለማውጣት ‹‹ፈስ ፈሶ ፈስ አራራ፣ ቆርጦ ቆርጦ ደም ያሳራ፣ ደሙ ሲረጋ በለው ባለንጋ፡፡ . . . ያጤ መስቀል ሲንቀለቀል የፈሳውን ልቡን ይንቀል›› ይባላል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች