የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ጌታቸው አስፋው፣ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቃለ ምልልስ ላደረገላቸው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተናገሩት፡፡ መንግሥት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለነዳጅ የሚያደርገውን ድጎማ በሒደት የሚያነሳ ከሆነ የዋጋ ንረቱ ላይ የሚኖረው አሉታዊ ሚና ምንድነው? ተብለው ለተጠየቁት የኢኮኖሚ ባለሙያው በሰጡት ምላሽ፣
የዋጋ ንረቱ 50 በመቶ ከደረሰ ግሽበት ይከሰትና ለኢኮኖሚው አሥጊ ስለሚሆን መንግሥት እንዲህ ዓይነቱ ነገር እንዲፈጠር ይፈልጋል ብዬ አላምንም ብለዋል። አሜሪካም ብትሆን ነፃ ኢኮኖሚ ሥርዓት የምትከተል ብትሆንም ለስንዴ ምርት ትደጉማለች ያሉት አቶ ጌታቸው፣ እኛም አገር ፍልስፍናዬ ነፃ ገበያ ሥርዓት ነው ተብሎ በአንዴ ድጎማ ይነሳል ብዬ አላምንም፤ ወደዚያ ቢገባ ደግሞ ቀውስ ነው የሚያመጣው ሲሉም አክለዋል።