Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  Homeስፖንሰር የተደረጉከትርፍ ይልቅ አገልግሎትን ያስቀደመው ታምሪን ሞተርስ በአውቶሞቲቭ ዘርፉ መልካም ስም የማስቀመጥ ጉዞ

  ከትርፍ ይልቅ አገልግሎትን ያስቀደመው ታምሪን ሞተርስ በአውቶሞቲቭ ዘርፉ መልካም ስም የማስቀመጥ ጉዞ

  Published on

  - Advertisment -

  ሱዙኪ ታምሪን ሞተርስ ከሚያስመጣቸው ተሽከርካሪዎች ግምባር  ቀደሙ እና ዋነኛው ነው፡፡ሱዙኪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማና ተፈላጊ ከሆኑ የመኪና አምራቾች አንዱ ሲሆን፣ ዘመኑን የዋጁ የቤት አውቶሞቢሎች ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርብ ነው፡፡የጃፓኑ ኩባንያ የሚፈበርካቸው መኪኖች ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ሚሊዮን ደንበኞች የሚገለገሉባቸው፣ ጥራትን ከዋጋ፣ ምቾትን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ መሆናቸው ነጋሪ የሚያሻው ጉዳይ አይደለም፡፡

  ለአካባቢ ሥነ ምህዳር ምቹ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ከሚያመርተው የሱዙኪ ኩባንያ ጋር የሚሰራው ታምሪን ሞተርስ፣ ዓይነትና አማራጨ ብዙ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ ከጀመረ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ታምሪን የደንበኞቹን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ለገበያ ከሚያቀርባቸው የሱዙኪ መኪኖች ውስጥ ቪታራ፣ ባሌኖ፣ ዲዛይር፣ ሱፐር ኬሪ፣ አልቶ 800፣ ሲያዝ፣ ኤርቲጋ፣ስዊፍት፣ ኤስ ፕሬሶ እንዲሁም ሌሎች ሞዴሎች ይገኙበታል፡፡

  ወቅትን የጠበቀ ጥገና እንዲሁም ተፈላጊውን የመኪና ግብዓት ለአውቶሞቢሎች ማሟላት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን የሚረዳው ታምሪን ሞተርስ፣ ለውድ ደንበኞቹ አስፈላጊ የሆኑ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በበቂ መጠን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ስለማቅረቡ ደንበኞች ሕያው ምስክር ናቸው፡፡

  ታምሪን ከሱዙኪ ሞተርስ ኩባንያ ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ተፈላጊ የሆኑትን አውቶሞቢሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች ለማቅረብ ባደረገው ከፍተኛ ትጋት ስኬታማ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት በቅቷል፡፡በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመራጭነታቸው ጎልቶ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ከሚንሸራሸሩት የተለያዩ ሞዴል የሱዙኪ ተሽከርካሪዎች አቅርቦት ጀርባ ታምሪን የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡

  ታምሪን የሚያቀርባቸው አውቶሞቢሎች በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እንዲጎላ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ፡ በቂ የመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦቱ፣ እንዲሁም ፈጣን የድህረ ሽያጭ አገልግሎቱ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በተለይም የድህረ ሽያጭ አገልግሎቶች የሚባሉትን የመለዋወጫ እንዲሁም የጥገና አገልግሎት አቅርቦቶችን በተጠቃሚው ፍላጎት ልክ በማሳደግ፣ የሱዙኪ አውቶሞቢሎች በዚህ ወቅት ካላቸው ስርጭት በበለጠ በስፋት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲገቡና ተጠቃሚው እጅ እንዲደርሱ ማድረግ የታምሪን ዋነኛ ተልዕኮ ነው፡፡

  በሌላ በኩል የሱዙኪ መኪና አምራች ኩባንያ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ከማምረት ባሻገር ጊዜው የሚጠይቀውን በኤሌክትሪክ እንዲሁም በነዳጅም ሆነ በኤሌክትሪክ  የሚሰሩ መኪኖችን የማምረት ጥናት ከማድረግ አልፎ የፈበረካቸው ምርቶች በቅርቡ በታምሪን ሞተርስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡በጠቅላላው ታምሪን አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ከጃፓኑ ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ ያለውን የገበያ ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

  ታምሪን የተሰማራባቸውን ዘርፎች ዘመናዊ በሆነ የቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚመራ፣የደንበኞች ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ምርቶችን የሚያቀርብ፣ እንዲሁም  ምስጉን ማናጅመንትና ሰራተኞቹን ደጀን አደርጎ አገልግሎቱን የሚያዳርስ ድርጅት ነው፡፡

  Suzuki Ethiopian Tamrin Motors Ethiopia Ethiopian Reporter

  የታምሪን ተደራሽነት ከግለሰብ እስከ ድርጅት

  ሰፊ የሚባል የተሽከርካሪ ፍላጎት ባለው የኢትዮጵያ አውቶሞቲቭ ገበያ፣ ታምሪን ሞተርስ ከግለሰብ አንስቶ ከበርካታ ድርጅቶች ጋር በጋራ የሚሰራ ሲሆን፤ የባንክ፣ ኢንሹራንስ፣ አየር መንገድ ሰራተኞች በድርጅቱ አማካኝነት ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለገበያ የሚቀርቡትን የሱዙኪ መኪኖችን ምርጫቸው በማድረግ ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡

  የሱዙኪ መኪናዎች ከሌሎች መኪኖች የተለየ ከሚያደርጋቸው አማራጮች ውስጥ ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የጃፓን መኪኖች መሆናቸው ሲሆን፣ ከዚህ ባሻገር በአገልግሎት ወቅት የሚጠይቁት ወጪ ዝቅተኛነቱ ሌላው የሚነሳ ልዩ መገለጫቸው ነው፡፡ከጥገና አኳያ እነዚህ መኪኖች መደበኛ ሰርቪሳቸው ርካሽ የሚባል ሲሆን፣ የሚቀየሩ ወይም የሚተኩ የመኪና አካሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ይቻላል፡፡

  የሱዙኪ አውቶሞቢሎች ስሪት ለኢትዮጵያ መልክዓምድር የተስማማ ሲሆን፣ አብዛኛው የመኪናው ክፍሎች ፋይበር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አደጋ በሚያጋጥምበት ወቅት የተጎዳውን ክፍል በቀላሉ መቀየር ይቻላል፡፡በጠቅላላው የሱዙኪ መኪኖች ቀላል(ኮምፓክት) ፣ ለፓርኪንግ አመቺ፣ነዳጅ ቆጣቢ መሆናቸው ልዩ ባህሪያቸው ነው፡፡  

  ለአብነትም በታምሪን ከሚቀርቡት የሱዙኪ አውቶሞቢሎች “አልቶ 800” አንዷ ስትሆን፣ በጣም ኮምፓክት የሆነች፣ ለፓርኪንግ አመቺ፣ ነዳጅ ቆጣቢ እና ተመራጭ ከሆኑትና በቁጥርም በርከት ብለው ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡት አውቶሞቢሎች ውስጥ ትጠቀሳለች፡፡ እንዲሁም ሱዙኪ ኢርቲጋ እስከ 7ት ሰው መጫን የሚችል ባለ ሙሉ አማራጭ የቤተሰብ መኪና በማቅረብ ሰፊ ተቀባይነት አግኝታል፡፡

  በቅርቡ የተመረቀው የታምሪን ማሳያ ማዕከል (ሾውሩም) እና ቀጣይ ዕቅዶች

  Ethiopian-Reporter-Tamrin-Motors

  ታምሪን ሞተርስ በሰኔ ወር ማጠናቀቂያ ተጨማሪ የደንበኞቹን ፍላጎት የሚያረካበት አገልግሎት ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም ከመገናኛ ወደ ኢምፔሪል ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ህንፃ ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ አሰራር መሰረት  የተሰራው  የሱዙኪ መኪኖች ማሳያ (ሾውሩም) ነው፡፡

  የአውቶሞቢል ማሳያ ማዕከል (ሾውሩሙ) ሁሉንም ዓይነት ሞዴል መኪኖችን በአንድ አዳራሽ (ስፍራ) ማሳየት የሚችል ሲሆን፣ ይህም ማለት በአንድ ጊዜ ከ15 እስከ 16 የሚደርሱ የተለያዩ ሞዴል የሱዙኪ መኪኖችን ለእይታ ለማቅረብ የሚያስችል ነው፡፡

  ታምሪን ሞተርስ ያስመረቀው ሾውሩም ከተለያየ የከተማዋ አቅጣጫ  የሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች እንዲሁም ደንበኞች በቀላሉ ሊመለከቱት በሚችሉበት አካባቢ የተገነባ ሲሆን፣ ውስጣዊ አሰራሩም ደንበኛን በሚማርክ ዲዛይን የታነፀ ነው፡፡

  ከመለዋወጫ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከበቂ በላይ በሚባል ደረጃ የመለዋወጫ ዕቃዎች ሳሪስ አደይ አበባ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ይገኛል፡፡በዚህ ማዕከል ከክምችት በተጨማሪ የድህረ ሽያጭ፣ የጥገና  አገልግሎቶች ይሰጣሉ፡፡ይህ ብቻ ሳይሆን የአውቶሞቢል ሞባይል ጥገና አገልግሎት በታምሪን ሞተርስ ከሚሰጡ የድህረ ሽያጭ አገልግሎቶች አንዱ ሲሆን፣ ደንበኞች በእጅ ስልካቸው ደውለው ባሉበት አካባቢ የጥገና አገልግሎት የሚያገኙበት አገልግሎት ነው፡፡

  ታምሪን ሞተርስ በክልል ዋና ዋና ከተሞች ተደራሽ ለመሆን ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ከየትኛውም የአገሪቱም ሆነ የዓለም ክፍል የሚገኙ ደንበኞች ስለታምሪን ሞተርስ አገልግሎት አሁናዊ መረጃዎችን የሚያቀርብበት ድረገፅ እንዲሁም ሌሎች የፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም የማህበራዊ መረጃ ትስስር ገፆች አሉት፡፡

  Suzuki LogoTamrin-Motors

  የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው እርጅና የተጫጫናቸው አጎታቸውን ለመጠየቅ ቢሄዱም ሚኒስትሩ ራሳቸው ተጠያቂ ሆነዋል]

  ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ ክቡር ሚኒስትር? ልትመዛት ያሰብካት ነገር አለች ማለት ነው? እንዴት? ክቡር ሚኒስትር ብለህ ጠራኸኛ?! ክቡር...

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ ንፁኃን በምሥራቅ ወለጋ መገደላቸው ተሰምቷል፡፡...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን በ2.3 ቢሊዮን...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ ጊዜ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ...

  ተመሳሳይ

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው የፔይሊንክ ፔይመንት ፕሮሰሲንግ አክሲዮን ማህበር...

  የጦርነት ቀጣና ውስጥ ያለፉ አካባቢዎች የውኃ አቅርቦት ተደራሽ የማድረግ ትልም

  ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በአማራ ክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ላይ በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ተደራሽ...