Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትክለቦች ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ ያገኙበት የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ

ክለቦች ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ ያገኙበት የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ

ቀን:

የጨዋታ ማጭበርበርን ለመግታት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል

የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮንነት መጠናቀቁን ተከትሎ በውድድር ዘመኑ ለተካፈሉት ክለቦች፣ ለአሸናፊዎች እንደየደረጃቸው፣ ለኮከብ ተጫዋቾችና አሠልጣኝ፣ ለኮከብ ዳኞችና ውድድሩን ላስተናገዱ ስታዲየሞች የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ አበርክቷል፡፡

የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ዓርብ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ፕሮግራም፣ ከስፖንሰሮቹ ቤትኪንግና ዲኤስ ቲቪ ያገኘውን ገንዘብ ለክለቦቹ የሚገባቸውን የአባልነት ትርፍ ክፍያ ክፍፍል በውድድር ዓመቱ ባስመዘገቡት ደረጃና ውጤት መሠረት እንዲከፈላቸው አድርጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚሁ መሠረት ፕሪሚየር ሊጉን በበላይነት ያጠናቀቀውና የዋንጫ ባለቤት ለሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ 10,994,819 ብር ሲከፈለው፣ ሌሎቹ ክለቦቹ ባስመዘገቡት  ውጤት በደረጃ ቅደም ተከተል መሠረት ሁለተኛ ለሆነው ፋሲል ከነማ 10,774,922 ብር፣ ሲዳማ ቡና 10,555,26 ብር፣ ሐዋሳ ከተማ 10,335,130 ብር፣ ወላይታ ድቻ 10,115,233 ብር፣ ኢትዮጵያ ቡና 9,895,337 ብር፣ አርባ ምንጭ ከተማ 9,675,440 ብር፣ ወልቂጤ ከተማ 9,455,544 ብር፣ መከላከያ 9,235,648 ብር፣ ሐዲያ ሆሳዕና 9,157,51 ብር፣ አዳማ ከተማ 8,795,855 ብር፣ ባህር ዳር ከተማ 8,575,959 ብርና ድሬዳዋ ከተማ 8,356,000 ብር ተከፍሏቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ታችኛው ሊግ የወረዱት አዲስ አበባ ከተማ ስምንት ሚሊዮን ብር ሲከፈለው፣ ሰበታ ከተማና ጅማ አባ ጅፋር እያንዳንዳቸው ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ አግኝተዋል፡፡

የክፍያውን አሠራር አስመልክቶ ሊግ ካምፓኒው፣ ተሳታፊ ክለቦች ከስፖንሰሮች ከሚገኘው ገንዘብ 60 በመቶ እኩል እንዲከፋፈሉ ከተደረገ በኋላ፣ ቀሪውን 25 በመቶ ደግሞ ባስመዘገቡት ውጤትና ደረጃ መሠረት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ ሊግ ካምፓኒው ለጽሕፈት ቤት አገልግሎት የሚውል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ፍፃሜውን ሰኔ 24 ቀን ያደረገውን የሊጉን ጨዋታዎች ያስተናገዱት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የድሬዳዋ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና የባህር ዳር   ስታዲየሞች እያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊዮን ብር አግኝተዋል፡፡

ከክለቦች የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ በውድድር ዓመቱ በኮከብ ተጫዋችነት ጋቶች ፓኖም 210 ሺሕ ብር፣ በኮከብ አሠልጣኝነት ዘሪሁን ሸንገታ 200 ሺሕ ብር፣ በኮከብ ግብ ጠባቂነት ቻርለስ ዩክዋ 150 ሺሕ ብር ሦስቱም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ፣ በከፍተኛ ጎል አግቢነት የሐዋሳው ይገዙ ቦጋለ (በ16 ጎል) 200 ሺሕ ብር፣ ‹‹ተስፈኛ በረኛ›› በሚል የጅማ አባ ጅፋሩ አልዓዛር ማርቆስ 105 ሺሕ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በምስጉን ዋና ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለ ኢየሱስ ባዘዘውና በምስጉን ረዳት ዳኝነት ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው እያንዳንዳቸው 105 ሺሕ ብር ተሸልመዋል፡፡

የሽልማት ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ ከጨዋታ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ የሊግ ካምፓኒው የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እንደ ‹‹የጨዋታ ማጭበርበር ፈጽመዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ክለቦች በጥርጣሬ ደረጃ ቢኖሩም እንኳ ዕርምጃ ለመውሰድ ረዥም ጊዜ የሚጠይቅ ነው፤›› ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው፣ ምክንያቱንም ሲገልጹ ሰዎች በእንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚሳተፉበት መንገድ ራሱን የቻለ ክትትልና ጥናት የሚጠይቅ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

አክለውም፣ ‹‹ድርጊቱን የፈጸሙ ለመኖራቸው ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥሉ ነገሮች አሉ፡፡ በመሆኑም ጥርጣሬዎችን ብቻ ይዞ ነገሩን በሕግና በደንብ ዕርምጃ ለመውሰድ ከባድ ነው፡፡ ምክንያቱም ጥርጣሬው በቀጣይ ለሚደረጉ ክትትልና ጥናት መነሻ ካልሆነ በሕግ ፊት ማስረጃ ሊሆን ስለማይችል ነው፤›› ብለዋል፡፡

ችግሩ አሁን ባለው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ለቀጣዩ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል፣ ሊግ ካምፓኒው የተቻለውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርግ የተናገሩት የመቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣ ‹‹ከዚህ ሒደት ተነስተን በሚቀጥለው ዓመት ምን እናድርግ? ደንባችን ውስጥ ምን ዓይነት ሕግ እናካትት? የሚለውን እናያለን፤ ምክንያቱም ወደፊት ወራጆች እንዴት ይውረዱ የሚለው በራሱ እጅግ አሳሳቢ ጥያቄ ስለሚሆን ነው፤›› ሲሉ ደምድመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...