Sunday, January 29, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ አልቻለም ተብሎ መወቀሱ አልተዋጠልኝም እያሉ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር እየተወያዩ ነው]

 • እንዴት መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ አልቻለም ይባላል? መንግሥት ስንት ነገር እያደረገ እንዴት ይወቀሳል?
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር? 
 • አንተም ጥያቄ አለህ?
 • ለመወያየት እንጂ እንዳሰቡት አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዴት እንዲህ አልክ? 
 • ለማለት የፈለግኩት ምን መስልዎት ክቡር ሚኒስትር …
 • ተወው … መንግሥት አማፂውን ቡድን ለመደምሰስ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ላይ መሆኑ እየታወቀ መወቀሱ ገርሞኝ ነው ጥያቄውን ያነሳሁት። 
 • ቢሆንም ክቡር ሚኒስትር አንድ አካባቢ ላይ በተደጋጋሚ ዜጎች ሲገደሉ ጥያቄ መፈጠሩ አይቀርም።
 • እሱን ችግር ለመቅረፍ አይደለም እንዴ ዘመቻ የተጀመረው?
 • እሱ ትክክል ነው ነገር ግን አማፂው ቡድን በተለመዱት አካባቢዎች ነዋሪዎች ላይ የአጠፋ ጥቃት እንደሚሰነዝር ታስቦ ጥበቃ መደረግ ነበረበት የሚል ወቀሳ ነው ማኅበረሰቡ የሚያነሳው። 
 • እየታገልነው ያለው ታጣቂ ርህራሄ ያልፈጠረበት መሆኑን አትዘንጋ እንጂ። አልሰማህም እንዴ መንግሥት የገለጸውን?
 • ምን?
 • ይህ ቡድን ሰሞኑን በአንድ አዛውንት ላይ ስለፈጸመው ጭካኔ? 
 • ምን አደረገ?
 • ልጃቸው የዚህ ቡድን አባል መሆኑን ያወቁ አንድ አባት ነገሩን ለመንግሥት በማሳወቅ በግቢያቸው የተቀበረ የጦር መሣሪያም እንዲወጣ ያስደርጋሉ። 
 • አዎ። ስለዚህ ጉዳይ ሲገለጽ ሰምቻለሁ።
 • ሰምተሃል አይደል? አባት መጠቆማቸውን የሰማው ልጃቸው አባቱን ከነቤታቸው ነው ያቃጠለው። 
 • ክቡር ሚኒስትር መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነት እያስጠበቀ አይደለም ተብሎ የሚወቀሰው ለዚህ ነው።
 • እንዴት? 
 • እኚህ አባት ኃላፊነታቸውን ሲወጡ መንግሥት ግን ኃላፊነቱን አልተወጣም። 
 • መንግሥት ምን ማድረግ ነበረበት?
 • አባት ልጃቸው ማመጹን በማሳወቅ የቀበረውን የጦር መሣሪያ ለመንግሥት እንደጠቆሙ፣ አማፂው ቡድን ሲሰማ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ከባህሪው አንፃር መገመት ቀላል ነው። 
 • እና?
 • ስለዚህ መንግሥት ኃላፊነታቸውን ለተወጡት አባት ጥበቃ በማቆም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባ ነበር።
 • መንግሥት ይህ እንደሚከሰት አላወቀማ?
 • ማወቅ ነበረበታ ክቡር ሚኒስትር። መንግሥት አይደል እንዴ? 
 • እሱስ ልክ ነው። 
 • እሱ ብቻ አይደለም ክቡር ሚኒስትር?
 • ሌላ ምን አለ?
 • እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በፍፁም ለሕዝብ መገለጽ አልነበረበትም። 
 • ለምን? 
 • ይህንን ክስተት እንዲሰማ የተደረገ ማኅበረሰብ ፍርሃት ውስጥ ነዋ የሚወድቀው። ይህ ብቻ አይደለም…
 • እ…
 • ነግ በእኔ ብሎ ማኅበረሰቡ እንዲሰጋና መንግሥትን እንዳይተባበር የሚያሰንፍ መረጃ ነው።
 • እህ…
 • እንዲህ ዓይነት መረጃ በፍፁም መለቀቅ አልነበረበትም።
 • መንግሥት ነገሩን በዚህ መንገድ የተረዳው አልመሰለኝም። 
 • ግን መረዳት ነበር።
 • ኦ….ኦ እንደዚያ አልተረዳነውም በቃ! ደግሞ ተጠንቀቅ?
 • ምን አጠፋሁ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዲህ ያለ ነገር ሌላ ቦታ እንዳታወራ!

[ክቡር ሚኒስትሩ የእረፍት ቀናቸውን ከመኖሪያ ቤታቸው ሳይወጡ ማሳለፋቸው ግራ ያጋባቸው ባለቤታቸው መጠየቅ ጀመረዋል]

 • ዛሬ ከቤትም አልወጣህ በሰላም ነው? 
 • ሰላም ነው ትንሽ ዕረፍት ማድረግ አስፈልጎኝ ነው። 
 • ግን ዕረፍት እያደረክ አይመስልም?
 • እንዴት?
 • ለረዥም ሰዓት ፀጥ ብለሃል … ያሳሰበህ ነገር አለ እንዴ?
 • እረ በጭራሽ። የለም!
 • ለነገሩ መጠየቅ አልነበረብኝም። 
 • ለምን?
 • በርካታ ችግርና ቀውስ ያለበት አገር አመራር ሆኖ አለመጨነቅና አለማሰብ አይቻልም ብዬ ነው። 
 • እረ በጭራሽ። ዕረፍት ማድረግ አሰኝቶኝ ነው እያልኩሽ?
 • እንዲያውም ዛሬ ልጠይቅ እስኪ?
 • ምን? ጠይቂኝ።
 • አሁን ካለንበት ሁኔታ እንቅልፍ የሚነሳህ የሚያሳስብህ ነገር ምንድን ነው? 
 • ጭራሽ እንቅልፍ የሚነሳ ነገር? እውነት እልሻለሁ ምንም የሚያሳስበኝ ነገር የለም። 
 • በአገሪቱ ብዙ ችግር እያለ እንዴት የሚያሳስብህ ነገር አይኖርም? ቢያንስ እያሻቀበ ያለው የኑሮ ውድነትና የሕዝቡ ችግር አያሳስብህም? 
 • የኑሮ ውድነት በኢትዮጵያ ብቻ የተከሰተ ችግር እኮ አይደለም? 
 • እንዴት?
 • ተመልከች አሜሪካን። ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ገጥሟቸዋል። አውሮፓውያኑም ቢሆኑ በነዳጅ አቅርቦት ችግርና በዋጋ ግሽበት እየተሰቃዩ ነው።
 • የእኛ አገር ግን የተለየ ነው። 
 • ግሽበት ግሽበት ነው፣ በምን ይለያል? 
 • እኛን ግሽበት ብቻ አይደለም እየፈተነን ያለው። በየአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የለም፣ ዜጎች ያለምክንያት ይገደለሉ … ብዙ መከራ አለ?
 • ልክ ነው ግን ሌሎች አገሮችም በተመሳሳይ እየተሰቃዩ ነው። ለምሳሌ ሰሞኑን በጃፓን የተከሰተውን ተመልከች።
 • ጃፓን ምን ተከሰተ?
 • የቀድሞ የአገሪቱ መሪ በአደባባይ ንግግር እያደረጉ ነው በጥይት የተገደሉት። በአውሮፓም ተመሳሳይ ችግር ነው ያለው።
 • እሱ ድንገተኛ ክስተት ነው። በዚያ ላይ እነሱ የተረጋጋ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያሉት።
 • አይምሰልሽ። የተረጋጋ ፖለቲካ ቢኖር የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ለምን ከሥልጣን ይወርዳሉ? ሩቅ ሳትሄጂ በሱዳን ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት አታስተውይም? 
 • በል ተወው!
 • ለምን? ምነው? 
 • የእኔ ጥያቄ ስለኢትዮጵያ ነበራ? 
 • እና?
 • አንተ ግን እየመለስክልኝ ያለኸው ስለሌላ አገር ነው።
 • እያነፃፀርኩልሽ እኮ ነው?
 • አይ ይቅርብኝ። ባትመልስልኝም ይገባኛል።
 • ምኑ ነው የሚገባሽ?
 • አትናገረውም እንጂ የአገራችን ሁኔታ በጣም እንደሚያሳስብህ ይገባኛል። 
 • እንዴት?
 • እንደሚያሳስብህ ብቻ ሳይሆን፣ ከሚያስጨንቅህ ሐሳብ ምን እረፍት እንደሚሰጥህ አውቃለሁ።
 • ምንድን ነው?
 • ችግኝ መትከል። 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...

ከውጭ ይገቡ የነበሩ 38 ዓይነት ምርቶች እንዳይገቡ ዕግድ ተጣለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 38 ከውጪ የሚገቡ ምርቶች ላይ ዕገዳ...

የአየር መንገድ ተጓዦች በሻንጣ የሚያስገቡትን የልብስና የጫማ ብዛት የሚገድብ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

ከቀረጥ ነፃ ይገቡ የነበሩ ዕቃዎች 87 በመቶ እንዲቀንሱ ተደርጓል መንገደኞች...

ኢትዮጵያ በ2023 የሚኖራት የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለ18 ቀናት ግዢ መፈጸሚያ ብቻ እንደሚሆን አይኤምኤፍ ተነበየ

ኢትዮጵያ በ2023 የሚኖራት የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለ0.6 ወር ወይም...
- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...

ለልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ተፈቀደ

የገንዘብ ሚኒስቴር በማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በሎጀስቲክስ፣ በኮንስትራክሽን፣ የባለኮከብ ሆቴሎች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ምን ገጥሞህ ነው? ስምምነቱን ጥሰውታል ክቡር ሚኒስትር? ኧረ ተውው ተረጋጋ፡፡ እሺ ክቡር ሚኒስትር ይቅርታ... ደንቆኝ እኮ ነው። ስምምነቱን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ለከተማ አስተዳደሩ እንድ ሹም በቢሮ ስልካቸው ላይ ደጋግመው ቢደውሉም ሊያገኟቸው ስላልቻሉ ወደ እጅ ስልካቸው ሞከሩ] 

ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ትላንት የቢሮ ስልክዎ ላይ ብደውል ለሥራ ወጥተዋል ተባልኩ፣ ዛሬም ስደውል ለሥራ ወጥተዋል ተባልኩ። ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር ቢሮ አልገባሁም ነበር። እኔ ሳላውቅ የጀመሩት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ጋር ስለ ጫካ ፕሮጀክት እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ላቀረብነው የውይይት ጥያቄ ፈቃደኛ ስለሆኑና በአጭር ቀጠሮ በመገናኘታችን ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በጭራሽ ምስጋና አያስፈልገኝም። ተቃዋሚ ፓርቲ ስትባሉ ብትቆዩም እኛ ስንመጣ ተፎካካሪ ያልናችሁ...