Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹አቤ›› ወደ ‹‹አበበ›› የተለወጠበት ገጠመኝ

ትኩስ ፅሁፎች

መሰንበቻውን በሰው እጅ የተገደሉት የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ፣ ከሰባት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ብለው ነበር። በቆይታቸውም ከሃምሳ ዓመት በፊት የዐሥር ዓመት ልጅ ሳሉ በቶኪዮ 1964 የኦሊምፒክ ማራቶንን ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፈውን የአበበ ቢቂላ ቤተሰብን ለማግኘት ችለው ነበር፡፡ የአበበ ልጅ የትናየት አበበም  በተገናኙበት ጊዜ የአባቱን ቶኪዮ ላይ 17 ቁጥር መለያውን ለብሶ ድል ሲያደርግ የሚያሳየውን ፎቶ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡

አበበ ቢቂላ በ1960 የሮም ኦሊምፒክ በባዶ እግሩ ባሸነፈ በአራተኛው ዓመት ጥቅምት 11 ቀን 1957 ዓ.ም. ባሸነፈ ጊዜ  ዝናው ከስሙ ጋር ተያይዞ በጃፓን እጅግ ናኝቶ ነበር።

ሺንዞ አቤ፣ አቤ የሚለው የተጸውዖ ስማቸው ከአበበ ጋር በመቀራረቡ የክፍል ጓደኞቻቸው አቤነታቸውን ትተው ‹‹አበበ›› እያሉ ሲጠሯቸው እንደነበር በአዲስ አበባ ቆይታቸው አውግተው ነበር፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ‹‹አቤ›› በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ደሴት ውስጥ ከሚነገር ‹‹ዓይኑ›› ቋንቋ የተገኘ ስያሜ ነው።

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች