Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን እንዲቀይር በተወሰነበት የሕክምና ተማሪን ጉዳይ በሚመለከት ኃላፊነት እወስዳለሁ...

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን እንዲቀይር በተወሰነበት የሕክምና ተማሪን ጉዳይ በሚመለከት ኃላፊነት እወስዳለሁ አለ

ቀን:

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ሳይንስ ትምህርቱን ለአራት ዓመታት ከተማረ በኋላ፣ መማር እንዳይቀጥል በታገደው ተማሪ ቢንያም ኢሳይያስ ላይ ለወሰነው ውሳኔ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡

ምንም እንኳን ተማሪው ሲመዘገብ ያለበትን የግራ እጅ እክል አሳውቆ የተመዘገበ ቢሆንም፣ ዩኒቨርሲቲው ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ የሕክምና ትምህርቱን በጤና ሳይንስ ኮሌጁ ሲያስተምር ቆይቶ፣ ማስቀጠል እንደማይችል ነግሮት ሌላ የትምህር ዓይነት እንዲመርጥ የሚያስገድድ ውሳኔ ወስኗል፡፡

በዚህም ምክንያት ለተፈጠሩት ችግሮችና ዩኒቨርሲቲው ላሳየው ቸልተኝነት ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የኮሌጁ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም ደነቀ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህም ከተማሪውና ከቤተሰቡ ጋር ውይይት ተደርጎ ተማሪው በሚፈልገው ነገር ድጋፍ ማድረግን ይሁን ካሳ መክፈል በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ኃላፊነት በመውሰድ እንደሚፈጽም ዶ/ር አንዱዓለም አስረድተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለተማሪው የሕክምና ትምህርቱን (Medicine) እንዲያቋርጥና ሌሎች ተጨማሪ አማራጮችን ያቀረበለት ቢሆንም፣ ተማሪው አራት የትምህርት ዘመናት ያሳለፈበትን የሕክምና ትምህርት (Medicine) ብቻ ተከታትሎ ለመጨረስ በመፈለጉ አልተቀበለውም፡፡

የቀረቡት አማራጮች አራት ዓመታት የተማራቸውን የትምህርት ዓይነቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደ ፋርማሲና ላቦራቶሪ ሳይንስ ትምህርቶችን በመቀጠል እንዲጨርስ፣ አሊያም ደግሞ በልዩ ሁኔታ በባዮ ሜዲካል ሳይንስ (Biomedical Science) አሁን ባለበት ደረጃ ዲግሪ ሰጥቶ ማስተርሱንም እንዲቀጥል ማድረግ ናቸው፡፡

ተማሪው እነዚህን ለመቀበል ባለመፈለጉ ወደፊት ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪውን በአራት ዓመታት በሕክምና (Medicine) ትምህርት አስተምሮ በመጨረሻ ወደ ቀዶ ጥገና (Operation) ትምህርት ላይ በሚገባት ጊዜ ነው ተማሪውን ሊከለክለው የቻለው፡፡ ጉዳዩ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተነገረ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ወቀሳ ገጥሞታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊትም ሌሎች ሁለት ተማሪዎች ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ የአካል ጉድለት ምክንያት ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ሳለ ማስቀየሩንም ዶ/ር አንዱዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ቀዶ ጥገናን ጨምሮ የተለያዩ የሕክምና ክንዋኔዎች ሙሉ የእጅ እንቅስቃሴን እንደሚፈልለጉ በማስረዳት፣ የተማሪ ቢንያም በሕክምና ትምህርት (Medicine) ማስቀጠል እንደሚቸገርም አክለው ገልጸዋል፡፡

‹‹ተማሪው አራት ዓመታት ሲቆይ ጉዳዩ ባለመታየቱ ለጠፋው ጥፋት ዩኒቨርሲቲውና ኮሌጁ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ በቀጣይም ምን መደረግ እንዳለበት ከተማሪውና ወላጆቹ ጋር ውይይት ተጀምሯል፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት በሌሎች ተማሪዎች ላይ የተፈጠሩት ችግሮችና የተማሪ ቢንያም ጉዳይ አገሪቱ ሐኪሞችን ‹‹እንደ ጎርፍ›› የማምረት ዕቅድ የያዘችበት ውጤት መሆኑንና በቅጡ መርጦ ያለማስተማር ችግር እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹በጊዜውም በዚህ ስትራቴጂ ላይ የሕክምና ባለሙያዎችና አመራሮችም ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተው ነበር፤›› ብለዋል፡፡

አገሪቱ ተማሪ ቢንያም በተመዘገበበት ጊዜ በነበረችበት ሁኔታ ምክንያትም ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉንም መሥፈርቶች ለማጣራት ስለመቻሉ ጥያቄ ውስጥ ነበር ብለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...