Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከፕሪሚየር ሊግ ለወረደው ክለቡ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ አዲስ አበባ...

ከፕሪሚየር ሊግ ለወረደው ክለቡ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ አዲስ አበባ ከተማ ገለጸ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ ለነበረው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ 106 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለምክር ቤቱ የዘንድሮን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ዓርብ ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት ለክለቡ ወጪ የተደረገውን የገንዘብ መጠን የገለጹት፡፡

ዘንድሮ አስተዳደሩ ካወጣው 5.94 ቢሊዮን ብር ውስጥ 106 ሚሊዮን ብር ለወራጁ ክለብ፣ እንዲሁም ሁለት ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ድጋፍ መደረጉ በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡

በ2013 ዓ.ም. ወደ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ፣ ባስመዘገበው 32 ነጥብ ብቻ መውረዱን አረጋግጧል፡፡

 ክለቡ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ተከትሎ ከፍተኛ ገንዘብ እንደተመደበለት ቢጠቀስም፣ በአንፃሩ የክለቡ ተጫዋቾች ወርኃዊ ደመወዛቸው በአግባቡ አልተከፈለንም በሚል አቤቱታ ሲያሰሙ መክረማቸው ይታወሳል፡፡

ሪፖርቱን ተከትሎ የስፖርቱ የቅርብ ሰዎች አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ያወጣው የተጋነነ ገንዘብና ክለቡ የተጓዘበት ግብ ለየቅል መሆኑን አንስተዋል፡፡

በርካታ የከተማ ክለቦች የመንግሥት ገንዘብ ቋት ላይ ተንጠልጥለው የሚሳተፉ ሲሆን፣ በየዓመቱ ለተጫዋቾች ከሚያወጡት ረብጣ ገንዘብ ጋር የሚመጣጠን መዋቅራዊ ለውጥ ሲያመጡ አለመስተዋላቸው ይጠቀሳል፡፡

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠናቀቁን ተከትሎ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 1 መከፈቱን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ አንድ ክለብ ለአራት ተጫዋቾች 35 ሚሊዮን ብር ድረስ ማውጣቱ ተስምቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ክለቦች ለአንድ ተጫዋች ዝቅተኛው አራት ሚሊዮን ብር ሲያወጡ፣ ከፍተኛው እስከ 10 ሚሊዮን ብር እያወጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፉ ከሚገኙት ክለቦች መካከል አብዛኞቹ ክለቦች መንግሥት በሚያደርግላቸው በጀት ላይ የተመሠረቱ ሲሆን፣ ዓመታዊ በጀታቸውን ከመልቀቅ በዘለለ ጠንከር ያለ ኦዲተር እንደሚያስፈልጋቸው የሚያነሱ አሉ፡፡

አብዛኞቹ ክለቦች ዓመታዊ ዕቅድና ግብ የሌላቸው እንደሆኑና ከፍተኛ ገንዘብ የሚያፈሱባቸው ተጫዋቾች ዕድሜያቸው የገፉና ልምድ አላቸው በሚል የዳቦ ስም ከአሠልጣኞች፣ ቡድን መሪዎች እንዲሁም ደላሎች ጋር በሚደረግ ሽርክና የሚከናውን ዝውውር እየተበራከተ መምጣቱ ምንጮች ለሪፖርተር ይናገራሉ፡፡

በዚህም መሠረት እግር ኳሱ ላይ የሚወጣው ገንዘብና በሜዳው ላይ የሚታየው ጨዋታ እንዲሁም አጠቃላይ የሊጉ ዕድገት ‹‹እንደ ካሮት ተክል ነው፤›› ሲሉ የሪፖርተር ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

የተጫዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወጣው ሠሌዳ መሠረት መከናወን እንዳለበትና ክለቦች የሚያስፈርሟቸውን ተጫዋቾች በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ማከናወን እንዳለባቸው ተቀምጧል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ክለቦች ይኼንን አካሄድ ጥሰው ተጫዋቾችን በራሳቸው መንገድ እንደሚያስፈርሙ ይነሳል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ክለቦች የአሠልጣኞችን ወርኃዊ ክፍያ፣ ከውጭ አገር የሚያስፈርሙትን ተጫዋችና ለአንዳንድ ተጫዋቾች በደፈናው የሁለት ዓመታት ክፍያ የሚከፍሉበትን ሒደት ግልጽ ያለማድረግ አካሄድ ባህል እያደረጉት መምጣታቸው ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የዝውወር መስኮት ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በስድስት ቀናት ውስጥ አራት ተጫዋቾች በፌዴሬሽኑ ተገኝተው ውላቸውን ማፅደቃቸው ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

ፋሲል ከነማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ባህር ዳር ከነማና መከላከያ በይፋ በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተጫዋቾችን ያስፈረሙና ውል ያደሱ ክለቦች ናቸው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...