Friday, September 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ሎተሪ በዓመት ለአምስት ሚሊዮን ደንበኞች የዲጂታል ሎተሪ ቲኬት ለመሸጥ ማቀዱን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በኢትዮ ቴሌኮም በኩል በዓመት ለአምስት ሚሊዮን ደንበኞች፣ የዲጂታል ሎተሪ ቲኬት ሽያጭ ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ።

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የሎተሪ ትኬትን በዲጂታል አማራጭ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያደረገ ሲሆን፣ ይህም ደንበኞቹ የሞባይል ስልካቸውን በመጠቀም የሎተሪ ትኬት የሚገዙበት አማራጭ መሆኑ ተገልጿል።

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች የሎተሪ ቲኬት በዲጂታል በቀላሉ መቁረጥ ያስችላል የተባለው ይህ ሥርዓት አድማስ ሎተሪ የተሰኘው ስያሜ ሲሰጠው፣ ዲጂታል ሎተሪውን በቴሌብር ወይም በ605 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መግዛት የሚያስችል መሆኑም ታውቋል።

የአንዱ ዲጂታል ቲኬት ዋጋ ሦስት ብር ሲሆን፣ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ዕጣ ያለው መሆኑን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ገልጸዋል።

በዚህም በወር ቢያንስ እስከ አምስት ሚሊዮን ደንበኞች በዲጂታል ሎተሪ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ፣ ብሔራዊ ሎተሪም እስከ 15 ሚሊዮን ብር ሽያጭ ለማድረግ ማቀዱን ገልጸዋል። በአዲሱ በጀት በዓመት እስከ 180 ሚሊዮን ብር ሽያጭ ለማከናወን ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል።

የሎተሪ ሽያጩ በዲጂታል መሆኑ ለውጭ አገር ዜጎች ዕድል የሚፈጥር ቢሆንም፣ አሁን ካለው ሕግ አንፃር ከአገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን መግዛት እንደማይችሉ አቶ ቴዎድሮስ አስረድተዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች