Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበችግር ውስጥ ያሉ ስደተኞች አገር ውስጥ መግባት

በችግር ውስጥ ያሉ ስደተኞች አገር ውስጥ መግባት

ቀን:

በርካታ ኢትዮጵያውን በተለይም ወጣቶች በኢመደበኛ መንገድ ድንበር አቋርጠው መሰደድ ከጀመሩ በርካታ አሠርታት ተቆጥረዋል፡፡ ዕድል የቀናቸው ካሰቡት ወይም ካላሰቡት አገር በሕይወት መድረስ ሲችሉ፣ ሌሎች የበረሃና የባህር ሲሳይ ሆነዋል፡፡

ጉዞ ተሳክቶላቸው ከአንዱ አገር የደረሱት ደግሞ ለጉልበት ብዝበዛ አሊያም ለእስር መዳረጋቸው የተለመደና በየጊዜው የሚነገር ክስተት ነው፡፡ ይህም ሆኖ ዛሬም በርካታ ኢትዮጵያውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ችግራቸውን ለማምለጥ ከተሳካ በመደበኛ፣ ካልተሳካ በኢመደበኛ መንገድ ድንበር አቋርጠው ይሰደዳሉ፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያን መዳረሻ ያደረጉ ስደተኞች በአብዛኛው ሰቆቃ የሚፈጸምባቸው፣ የሚገረፉና በየእስር ቤቱ የሚታጎሩ፣ በኋላም ተጠርንፈው ወደ አገራቸው የሚመለሱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ በሕይወት መቆየት ከቻሉት የአዕምሮና የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በማገገሚያ የሚቆዩ መኖራቸውንም ከዚህ ቀደም ሪፖርተር ጋዜጣ በተለያዩ ዘገባዎቹ አስተናግዷል፡፡

- Advertisement -

በችግር ውስጥ ያሉ ስደተኞች አገር ውስጥ መግባት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ኢትዮጵያውያን ወደ ኬንያ፣ ታንዛኒ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ የመን፣ ሊቢያ፣ ዑጋንዳ፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ሌሎች የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የመካለኛው ምሥራቅ አገሮችን መዳረሻ በማድረግ የሚፈጽሙትን ኢመደበኛ ጉዞ ለመቀልበስ በመንግሥትና በተለያዩ አካላት ጥረት ቢደረግም፣ ከችግሩ ግዝፈትና ስፋት አኳያ በሚፈለገው መጠን ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡

በተለይ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በሕገወጥ መንገድ የነጎዱና በዚያው ለሥቃይ የተዳረጉ፣ በሕጋዊ መንገድ ሄደውም እንደ ሕገወጥ ወደ በእስር ቤት የተወረወሩ፣ በዚህም ለሞት፣ ለበሽታ ለረሃብና ለሥቃይ የተዳረጉ ዜጎችን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጭምር ከወራት በፊት ሲዘግቡት ከርመዋል፡፡

ይህ ከመሆኑ አስቀድሞም በተለያዩ ጊዜያት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር የመመለስ ሥራ ያከናወነው መንግሥት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤት የታጎሩ ዜጎችን ከመጋቢት 2014 ዓ.ም. ወዲህ መመለስ ጀምሯል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫም፣ ከሳዑዲ ዓረቢያ ብቻ 102 ሺሕ ዜጎችን ለመመለስ በታቀደው መሠረት፣ ከመጋቢት እስከ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ 50 በመቶ ያህሉ መመለሳቸውን አስታውሰዋል፡፡

በእነዚህ ወራት በሳምንት ሦስት ጊዜ በአጠቃላይ 137 በረራዎችን በማድረግ  50 በመቶ ያህል ዜጎችን መመለስ መቻሉ፣ ከዕቅድ አንፃር የተሻለ ውጤት የታየበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

12 ሺሕ ዜጎችን ከአፍሪካና መካለኛው ምሥራቅ ለመመለስ መታቀዱን የገለጹት አምባሳደር መለሰ፣ ለዚህም ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በትብብር ይሠራል ብለዋል፡፡

12 ሺሕ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ሥራ የሚከናወነም ከታንዛኒያ፣ ከጂቡቲ፣ ከሱዳን፣ ከማላዊ፣ ከዚምባቡዌ፣ ከዛምቢያና ከኦማን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ማኒስቴር እንዳለው፣ በሳውዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገር በመመለስ ሥራው 50,337 ኢትዮያውያን ወደ ኢትዮጵያ  ተመልሰዋል።

በመጀመርያው ዙር ከሰባት እስከ አሥራ አንድ ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ 102,000 ዜጎችን ለመመለስ በተያዘው ዕቅድ መሠረትም፣ ከተመለሱት 50,337 ዜጎች ውስጥ 37,485 ወንዶች፣ 9,225 ሴቶች እና 3,628 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ሕፃናት መሆናቸውን አስታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎችም ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ሥራ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እየተሠራ ይገኛል ብሏል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...