Tuesday, November 28, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ቢሮው 70 ቢሊዮን ብር ከታክስ ገቢ እሰበስባለሁ አለ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከቴሌ ብር ጋር የበይነመረብ ክፍያ አስጀምሯል

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በተያዘው የበጀት ዓመት 70 ቢሊዮን ብር ከታክስ ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ይህም በ2014 ከተሰበሰበው በ15 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ቢሆንም ከባለፈው ዓመት የ18 ቢሊዮን ብር ዕድገት ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ያለ ጭማሪ ነው፡፡

ቢሮው ትናንት ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቴሌ ብር ጋር የበይነመረብ ታክስ ክፍያ ሥርዓት ያስጀመረ ሲሆን 289 ሺሕ የከተማዋ ግብር ከፋዮች በሥርዓቱ ውስጥ ተካተዋል፡፡ በአዲስ አበባ በአጠቃላይ 440 ሺሕ ግብር ከፋዮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም 340 ሺዎች የ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡ እነዚሁ በቴሌ ብር መክፈል የሚችሉት የ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ብቻ ሲሆኑ፣ እነሱም በዓመት በሦስት ቢሊዮን ብር ያነሰ ጠቅላላ ገቢ የሚያስገኙ ናቸው፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈሪ፣ ‹‹ሀ እና ለ›› በሒደት የ‹‹ሐ›› ውጤታማነት ታይቶ ይቀላቀላሉ፤›› ብለዋል፡፡

ግብር ከፋዮች ከዚህ በፊት በንግድ ባንክ ብቻ ይከፍሉ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ከቴሌ ብር ጋር ከሚሠሩት 13 ባንኮች ቀጥታ ከቤታቸው በሞባይል ቁርጥ ግብራቸውን አውቀው መክፈል ይችላሉ፡፡

አቶ ብሩክ አዳነ በኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር፣ ‹‹ከተቀሩት ባንኮች ጋር ሲስተም የማሳለጥ ሥራ እየተገባደደ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የቀበሌ ቤት ኪራይ፣ የቦታ ኪራይ፣ የሼዶች ኪራይ ክፍያና ሌሎችም የማዘጋጀ ቤት አገልግሎቶች በቅርቡ በቴሌ ብር ይጀመራሉ፡፡

በቅርቡ የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የጠየቀውን 100 ቢሊዮን ብር በጀት ፓርላማው ያፀደቀ ሲሆን፣ አስተዳደሩ ወጪውን በራሱ ገቢ ለመሸፈን መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

ከፀደቀው 100 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ 70 ቢሊዮኑ ከታክስ፣ እንዲሁም ቀሪው ደግሞ ከትራፊክ ቅጣትና ሌሎች የማዘጋጃ ቤት ገቢዎች ታቅዷል፡፡ የንብርት ግብርም (Property tax) በተያዘው 2015 ለመጀመር የታቀደ መሆኑን የመስተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት አቶ አብዲ ፀጋዬ ገልጸዋል፡፡

‹‹የንብረት ግብር የሕግ አግባብ ጉዳዮች ላይ እየተሠራ ነው›› ሲሉ አቶ አብዲ አስረድተዋል፡፡ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት ለተያዘው ዓመት ቢመድብም በተገባደደው የ2014 አፈጻጸሙ ግን ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት አጋጥሞት እንደበር ያሳያል፡፡ አስተዳደሩ ለ2014 በጀት 70.6 ቢሊዮን በጅቶ የነበረ ሲሆን የተጠቀመው ግን 49.7 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ ለዓመቱ ካስቀመጠው 2.5 ቢሊዮን ብር መጠባበቂያ በላይ ሄዶ 5.5 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን በዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ ቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች