Thursday, April 18, 2024

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር)ን ይቅርታ ጠየቀ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2012 በጀት ዓመት የኦዲት ግኝት ላይ ከተደረገ ውይይት ጋር በተያያዘ፣ የሚኒስቴሩ የቀድሞ ሚኒስትር ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) ለሥራ ይጠቀሙበት ከነበረ የስልክ ክፍያ ጋር በተያዘ ያስተላለፈው መረጃ ስህተት መሆኑን ገልጾ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይቅርታ የጠየቀው በተቋሙ የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበራ ጎዴቦ ማኔ፣ ‹‹ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከለቀቁ በኋላ፣ ለግል ስልካቸው 104 ሺሕ ብር እንዲከፈል በማድረጋቸው እንዲመልሱ ተደርገዋል፤›› በማለት የተናገሩት መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ዕትም በመውጣቱ ነው፡፡

መረጃው በሪፖርተር ከተዘገበ በኋላ ሒሩት (ፕሮፌሰር) ቅሬታ በማቅረባቸው ሚኒስቴሩ ለፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቆ፣ ፕሮፌሰሯ ተሹመውበት ከነበረው ተቋም ጋር ደብዳቤ ተጻጽፎ ለስልክ የተከፈለው ብር እንዲመለስ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቆ ዜናው እንዲስተካከልም ጠይቋል፡፡

ከዝግጅት ክፍሉ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የ2012 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት አዲስ ግኝትን አስመልክቶ የተደረገውን ውይይት፣ ሪፖርተር በግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ዕትሙ፣ ‹‹የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ለሚጠቀሙበት የመደበኛ ስልክ ጣሪያ እንዲወጣ ፓርላማው ጠየቀ›› በሚል ርዕስ ዘገባ ሠርቷል፡፡ በዘገባው ዝርዝር ውስጥ፣ ዘጋቢው ያነጋገራቸው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበራ ጎዴቦ ማኔ፣ የቀድሞ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት (ፕሮፌሰር) ተቋሙን ከለቀቁ ጀምሮ፣ ከሕግ ውጪ በሚኒስቴሩ ስም 109 ሺሕ ብር ለመደበኛ ስልካቸው መከፈሉንና በ2013 ዓ.ም. እንዲመልሱ በደብዳቤ ተጠይቀው ገንዘቡን መመለሳቸውን መናገራቸውን መዘገቡ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -