አዲሷ የዓለም ማራቶን ሻምፒዮኗ ጎተይቶም ገብረሥላሴ፣ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ውድድር ሰኞ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. አሸናፊ ከሆነች በኋላ የተናገረችው፡፡ በአሜሪካ፣ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ሻምፒዮና፣ የሻምፒዮኑን ክብረ ወሰን የሰበረችው ጎተይቶም በትግራይ የሚገኙትን ወላጆቿን አስታውሳ የተናገረችው በእንባ ተሞልታ ሲሆን፣ የዓለም ሻምፒዮን ክብርን መቀዳጀትን የገለጸችው በጣም ትልቅ ነገርና መግለጽ ከምችለው በላይ ነው በማለት ነው፡፡