Tuesday, December 5, 2023

የኮንትሮባንድ ንብረቶችን ለማስለቀቅ የሚሞክሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

በየክልሉ የሚያዙ የኮንትሮባንድ ንብረቶችን ለማስለቀቅ የሚሞሞክሩ የመንግሥት መዋቅር አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስጠነቀቀ።

በኢትዮጵያ የቁም እንስሳትና በሌሎችም በርካታ የኮንትሮባንድ ምርቶች እንደሚሸጡና ለዚህም የመንግሥት አካላት ጭምር ተባባሪ እየሆኑ እንደሚገኙ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጐፌ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ባላት የቁም እንሰሳት ብዛት ታዋቂ ብትሆንም በዘርፉ የወጪ ንግድ ተሳትፎዋ በጣም ዝቅተኛ ነው ያሉት አቶ ካሳሁን፣ ለዚህም ዋነኛው የኮንትሮባንድ መስፋፋት ነው ብለዋል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአገራችን የቁም እንስሳት በኮንትሮባንድ ወደ ጎረቤት አገሮች ይወጣሉ ሲሉም አክለዋል፡፡

ለራሳቸው ፍጆታ የቁም እንስሳትን ከሌሎች አገሮች በማስገባት የሚታወቁ ነገር ግን ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድ የሚያስገቡትን ለሌሎች አገሮች ኤክስፖርት በማድረግ በዘርፉ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መስመሩን ይዘው ይገኛሉ ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ቁጥር ብዛት ከመጠራት ውጪ ባላት የቁም እንስሳት ልክ ተጠቃሚ እየሆነች አይደለም ብለዋል።

ኮንትሮባንድን ለማስቀረት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ቅንጅት በመፍጠር በቁርጠኝነት እንደሚገኝና በ2015 በጀት ዓመት የፀረ ኮንትሮባንድ ሥራን አጠናክሮ መሥራት እንደሚጠበቅ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሁላችንም ኢትዮጵያ አገራችን በኮንትሮባንድ ምክንያት የምታጣውን ሀብት ማዳን ይገባል በማለት ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ሒደት በየክልሉ የሚያዙ ንብረቶችን ለማስለቀቅ የምትሞክሩ የመንግሥት መዋቅር አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ሲሉም አሳስበዋል።

የተሰየሙለትን አገራዊና መንግሥታዊ ዓላማ ወደ ግራ ብለው የፀረ ኮንትሮባንድ ሥራውን በማደናቀፍ፣ ኮንትሮባንድን ሕጋዊ በማስመሰልና ለኮንትሮባንዲስቶች ተባባሪ በመሆን ኮንትሮባንድ ዕድሜው እንዲረዝም እያደረጉ ያሉ አካላት አሉ፡፡ እነዚህን አካላት ከኮንትሮባንዲስቶች ለይተን ስለማናያቸው በያዝነው አዲስ በጀት ዓመት አበክረን እንፋለማቸዋለን ሲሉ አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡

የቁም እንሰሳትም ሆነ ማንኛውም የአገር ውስጥና የወጪ ንግድ ምርቶችን ኮንትሮባንድ በማስቆምና ግብይቱ በሕጋዊው የገበያ ሥርዓት ብቻ እንዲፈጸም ማድረግ ይገባልም ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -