Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ400 በላይ ቀዶ ጥገና በሠራው የማስተርስ ተማሪ ላይ ያስተላለፈው...

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ400 በላይ ቀዶ ጥገና በሠራው የማስተርስ ተማሪ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ እያነጋገረ ነው

ቀን:

የማሕፀን ሕክምና (gynecology) ስፔሻሊቲ ሐኪም ለመሆን የልዩ ማስተርስ ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ ጥቂት ወራት ሲቀሩትና መመረቂያ ጽሑፉን ሊያቀርብ በሚዘጋጅበት ጊዜ መመረቅ እንደማይችል ነግሮ ባሰናበተው ዶ/ር ታዘባቸው ውቤ ላይ በወሰደው ዕርምጃ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ሳይንስ ትምህርት ክፍል ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተነሳበት ነው።

ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በጠቅላላ ሐኪምነት (general practitioner) በ2006 ዓ.ም. ከተመረቀ ወዲህ በይርጋለም ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ በሐኪምነትና መምህርነት ለሁለት ዓመታት ሲያስተምር የቆየው ዶ/ር ታዘባቸው፣ ስፔሻላይዝ ለማድረግ የማሕፀን ሕክምናን በመምረጡ እዚህ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርቱን መከታተል ችሏል።

ሆኖም ግን ለአራት ዓመታት ተምሮ መመረቂያ ጽሑፉን በማዘጋጀት ላይ ሳለ ካለምንም ምክንያት ዓይኑን እንዲመረመር ትምህርት ቤቱ ያዘዘው ሲሆን፣ እሱም ይህን አድርጎ ሲጨርስ ዓይንህ ላይ ችግር ስላለብህ በዚህ ትምህርት መመረቅ አትችልም በማለት መመረቅ እንደማይችልና ሌላ ትምህርት እንዲማር አስገድዶታል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ስፔሻሊቲ ትምህርቱን በዚህ ሕክምና ኮሌጅ ውስጥ በመማር ላይ ሳለም የተወሰኑትን ከመምህራን ክትትል ጋር አብዛኛውን ግን ያለ ክትትል ለብቻው ከ400 በላይ ቀዶ ጥገናዎችን በማካሄድ፣ የወሊድ የሕክምና ሥራዎችን ሲያከናውን ነበር፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉን እያጠናቀቀ ከትምህርት መሰናበቱ ሲገለጽለትም በዘውዲቱ ሆስፒታል ተመድቦ በማገልገል ላይ ሳለ ነበር፡፡

መጀመርያ በተማሪዎች ተወካይ በኩል በመጣ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ከትምህርት ክፍሉ መሰናበቱ የተነገረው ዶ/ር ታዘባቸው፣ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊዎችን ወዲያው ማነጋገር እንደጀመረና በእነርሱ በኩልም መልስ ሲያጣ ወደ ዋናው ዩኒቨርሲቲ ድሕረ ምረቃ ክፍል አቤቱታ ማቅረቡን ይገልጻል፡፡ በዋናው ጊቢ በኩልም መልስ በማጣቱ ተስፋ በመቁረጥ አዲስ የትምህርት ዓይነት ለመማር የተለያዩ የኮሌጁን ትምህርት ክፍሎች ሊያስተምሩት እንደሚችሉ መጠየቅ ጀመረ፡፡

‹‹የሚገርመው በምን የትምህርት ዓይነት እንኳን፣ የመባረር ሥጋት ሳያጋጥመኝ መማር እንደምችል ጠይቄ ቀና መልስ ከኮሌጁ አላገኘሁም›› ሲል የገጠመውን  ይገልጻል፡፡

በ2013 ዓ.ም. መስከረም ወር አካባቢ እንደተሰናበተ ካወቀ በኋላም ለሰባት ወራት ሲከራከር ቆይቶ በመጨረሻም ቀዶ ጥገና በማይካሄድበት ነርቭ ሕክምና (Neurology) ትምህርት የሚያስተምረው ክፍል እንዲማር ፈቅዶለት መማር መጀመሩን ዶ/ር ታዘባቸው ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ዶክተሩ ከዚህም ስፔሻሊቲ ትምህርት ከተማረ በኋላ እንደማያሰናብቱት የተሰጠው ምንም ዋስትና የለም፡፡

የሕክምና ሳይንስ ኮሌጁ በበኩሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ምንም ማለት እንደማይመርጥ የገለጹት የኮሌጁ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዷለም ደነቀ፣ በአጠቃላይ እንደ ዩኒቨርሲቲና እንደ አገር ምን ማድረግ አለብን በሚለው ዙሪያ ላይ ትኩረት እየተደረገ እንደሆነ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የዶ/ር ታዘባቸው ጉዳይንም በሚመለከት ጉዳዩ ተጣርቶ ሚዲያው ማግኘት አለበት የሚሉትን ነገሮች ወደፊት እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡ ‹‹አሁን እየተፈጠረ ያለውን ነገር እንደ ‹‹ኦፖርቹኒቲ›› (ዕድል) ወስደነው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዩኒቨርሲቲዎችንና ሚኒስትሪዎችን አካቶ በጋራ መካሄድ ያለባቸውን ክርክሮችና ጉባዔዎችን ማካሄድ ይኖርብናል›› ሲሉ ዶ/ር አንዷለም ገልጸዋል፡፡ አሁን እየተሠራበት ባለው ግለሰቦችን ብቻ ካማከለ መፍትሔ ተላቆ አጠቃላይ ተማሪዎችን በሚመለከት መፍትሔ ለማምጣት እንደሚሠሩ ዶክተሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹የሕክምና ትምህርት ከቅበላ እስከ ምርቃት ድረስ እንዴት መሄድ አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ጨምሮ ከተማሪዎች መብት፣ የአካል ጉዳተኝነትና የሕሙማን መብትንና ደኅንነት እንዴት ይሁን ለሚለው ተወያይቶ መቀጠል ይኖርበታል፤›› ሲሉ ዶ/ር አንዷለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው በተፈጥሮ አንድ ዓይኑ የተንሸዋረረ ሲሆን በእሱ እምነት ግን ይህ የሕክምና ሥራውን ለመሥራት በምንም ሁኔታ እንደማያግደው ይገልጻል፡፡ በትምህርት ክፍሉ ትዕዛዝ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ተመርምሮ ባገኘው ውጤት በጣም ጥቃቅን የሆነ አረንጓዴና ቀይ ቀለሞችን የማንበብ ችግር እንዳለበት ተገልጾለት ነበር፡፡ ነገር ግን ዶክተሩ እዚያው ዳግማዊ ምኒልክ የዓይን ሕክምና ክፍል በራሱ ባደረገው ምርመራ ይህ የተባለው ችግር እንደሌለበት እንደነገረው ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ ይህንንም ለትምህርት ክፍሉ ሲያሳውቅ ያገኝ የነበረው መልስ ምንም ኃላፊነት መውሰድ እንደማይፈልጉ ነበር፡፡

ለዶክተሩ በጥብቅና እያገለገለው ያለው ጠበቃ አቶ ዳንኤል ፈቃዱ እንደሚገልጹት፣ በዚህ ዶ/ር ላይ ትምህርት ክፍሉ ያደረገው ድርጊት የአገር ሀብት ማባከን እንደሆነና ትምህርት ክፍሉም ውሳኔውን አጥፎ ተማሪውን መመለስ እንዳለበት ነው፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው በገጠመውም ጉዳይ የአካል ጉዳተኛ እንደማያስብለውና እሱ ለብቻው ተለይቶ ተመርምሮ ነው እንጂ፣ ማንኛውም በሥራ ላይ ያለም ዶ/ር ቢሆን ቢመረመር ከዚህ በላይ ችግሮች ሊገኝበት እንደሚችልም ጠበቃ ዳንኤል ከተለያዩ ዶክተሮች ጋር የደንበኛቸውን ጉዳይ በሚመለከት የደረጉትን ምክክር በመጥቀስ ገልጸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...