Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች አበረታች ቅመም በመጠቀሙ ቅጣት ተላለፈበት

የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች አበረታች ቅመም በመጠቀሙ ቅጣት ተላለፈበት

ቀን:

የመከላከያ እግር ክለብ ተጫዋች የሆነው አሌክስ ተሰማ ኃይሌ የፀረ አበረታች ቅመሞች የሕግ ጥሰት ፈፅሞ በመገኘቱ፣ ለአንድ ዓመት በማንኛውም የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጣለበት።

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን (ናዶ) በፕሪሚየር ሊጉ ተጫዋቾች ላይ እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 10 ቀን 2021 ባደረገው የአበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ምርመራ፣ የመከላከያ ተጫዋች የሆነው አሌክስ ተሰማ ኃይሌ የተከለከለ አበረታች ቅመም መጠቀሙን የሚያረጋግጥ ምልክት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።

ባለሥልጣኑ የምርመራውን ሒደት በተመለከተ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 23 ቀን 2022 ጀምሮ ተጫዋቹ በየትኛውም የእግር ኳስ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ጊዜያዊ ዕገዳ በመጣል፣ በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ተጨማሪ የምርመራና የማጣራት ተግባራትን ሲያከናውን ከቆየ በኋላ፣ ካቲኖን (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ አበረታች ቅመም የተጠቀመ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል ብሏል።

ስለሆነም አትሌት አሌክስ ተሰማ ኃይሌ የመጀመርያው ጊዜያዊ ዕገዳ ከተጣለበት፣ ማለትም እ.ኤ.አ. ከየካቲት 23 ቀን 2022 ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2023 ድረስ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር እንዳይሳተፍ ዕገዳ የተጣለበት መሆኑን በመግለጽ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተጫዋቹ ቅጣቱን ጨርሶ ዕገዳው እስኪነሳለት ድረስ በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ክትትል እንዲያደርግ ባለሥልጣኑ አሳውቋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን፣ በ2014 በጀት ዓመት አበረታች ቅመሞችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ሲያከናውን የቆየውን ተግባር ክንውን ይፋ አድርጓል፡፡

ባለሥልጣኑ በማኅራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፣ ተቋማዊ አቅም መገንባት፣ የሕግ ማዕቀፎችን መዘርጋትና ማሻሻል፣ ረቂቅ ፖሊሲን በማዘጋጀት፣ የአሠራር ሥርዓቶችን በመከለስ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህም በ2014 ዓ.ም. የውድድር ዓመት እግር ኳሱን ጨምሮ ለ533 ስፖርተኞች ምርመራ ማድረጉን በማሳያት ጠቅሷል፡፡

ባለሥልጣኑ የምርመራውን ውጤት በተመለከተ፣ የተወሰኑ አትሌቶች በዋናነት እግር ኳስና አትሌቲክስ ላይ የሕግ ጥሰት ሒደቶች ስለመታየታቸው ጭምር አስታውቋል፡፡

የስፖርት ፀረ አበረታች ቅመሞችን በመከላከል ረገድ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ለሚታመንባቸው፣ ማለትም የብሔራዊ ቡድንና የክለብ አሠልጣኞች እንዲሁም የአትሌት ማናጀሮችና ወኪሎች የተሳተፉበት መድረክ በማዘጋጀት ውይይት ማድረጉን ተናግሯል፡፡

በውይይቱ አትሌቶች በሕክምና ተረጋግጦ በሐኪም ፈቃድ ካልታዘዘላቸው በስተቀር የትኛውንም ድጋፍ ሰጪ ምግብ (መድኃኒቶችን) እንዳይጠቀሙ ማሳሰቢያ ስለመስጠቱ ጭምር ባለሥልጣን በመግለጫው አክሏል፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...