Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየድሬዳዋው ሚሌኒየም ፓርክ በታዋቂው ድምፃዊ አሊ ቢራ ተሰየመ

የድሬዳዋው ሚሌኒየም ፓርክ በታዋቂው ድምፃዊ አሊ ቢራ ተሰየመ

ቀን:

ለስድስት አሠርታት በሙዚቃዊ ሥራው ልዕልናን የተቀዳጀው ድምፃዊ አሊ ቢራ የትውልድ ከተማው ድሬዳዋ በስሙ ፓርክ ሰይሞለታል፡፡  ከዚህ ቀደም ሚሌኒየም ፓርክ ተብሎ የሚታወቀውን ፓርክ ‹‹አሊ ቢራ ፓርክ›› ተብሎ መሰየሙን ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር ናቸው፡፡ በፓርኩ ቅጥር ግቢ በነበረው ሥነሥርዓት ድምፃዊው አሊ ከባለቤቱ ጋር የተገኘ ሲሆን፣ በክብር እንግድነት የከተማዋ ሹማምንትን ጨምሮ የቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊና የቀድሞው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር መሐመድ ድሪር መገኘታቸውን ከድሬዳዋ ኮሚዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በ1954 ዓ.ም. የሙዚቃውን ዓለም የተቀላቀለው ድምፃዊው አሊ ቢራ፣ ከኦሮምኛ በተጨማሪ በአማርኛ፣ በሱማሊኛ፣ በአፋርኛ፣ በሐረሪ እና በዓረብኛ ቋንቋዎች የሙዚቃ ሥራዎችን መሥራቱ ይታወቃል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...