Tuesday, October 3, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ ነው]

በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው።

 • ክቡር ሚኒስትር…
 • እሺ …ቀጥል
 • አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ ሆኖ በልዩ ሁኔታ ልንወያይባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዲካተቱ ቢደረግ ለማለት ነው።
 • በልዩ ሁኔታ የሚነሳ ምን አጀንዳ አለ? 
 • ይኖራል እንጂ ክቡር ሚኒስትር …አለ!
 • አጀንዳ ማስያዝ ትችላለህ …ቀጥል።
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ሠግቻለሁ!
 • ሠግቻለሁ?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር …እኔ ፍርኃት አለኝ።
 • ፍርኃቱን ተወውና አጀንዳህን ለምን አታስይዝም?
 • ወደ እሱ ልመጣ ነው።
 • እሺ …ቀጥል 
 • ክቡር ሚኒስትር ፍርኃት አለኝ ያልኩት አጀንዳዬን ከነ ስሜቱ ለማስያዝ ፈልጌ ነው። የዛሬ ውይይታችን በዚህ መልኩ በግልጽ ካልተካሄደ መፍትሔው ይርቅብናል ብዬ አስባለሁ። 
 • ለምን ወደ አጀንዳህ አትገባም?
 • ወደዚያ እየመጣሁ ነው ክቡር ሚኒስትር። በቀዬው ለዓመታት ተቀምጠን ያልደፈረን አልሸባብ ከሰሞኑ በአገራችን ላይ ወረራ መፈጸሙ አስግቶኛል። አልሸባብ እንደዚህ ዓይነት ድፍረት ላይ ሲደርስ እኛ የት ነበርን? 
 • አጀንዳውን እንወያይበታለን ነገር ግን አንተ እንዳልከው ፍርኃት የሚጭር ወይም የሚያሠጋ አይደለም። 
 • እንዴት አያሠጋም ክቡር ሚኒስትር? 
 • አንተን ልጠይቅህ፣ ለምን ሥጋት ተፈጠረብህ?
 • አልሸባብ ምን ነበረ፣ እንዴት በዚህ ደረጃ ኢትዮጵያን ደፈረ የሚለውን ከጠየቅን ያሠጋል። በቀላሉ መታየት የለበትም ክቡር ሚኒስትር። 
 • አልሸባብ ምን ነበረ ማለት? አሸባሪ አይደለም እንዴ? በፊትም አሸባሪ ነው፣ አሁንም አሸባሪ ነው።
 • ትክክል ነው። ግን ቦምብ ከማፈንዳትና አጥፍቶ ከመጥፋት ውጪ አቅም ያልነበረው የሽብር ቡድን ነበር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ።
 • እና ምን እያልክ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር የአጥፍቶ መጥፋት ቦምብ በማፈንዳት የሚታወቅ ቡድን አድጎ አገር ለመውረር ሲንቀሳቀስ እኛ የት ነበርን? ተቋሞቻችን ምን ይሠሩ ነበር? 
 • ሥጋትህን ተረድቻለሁ ነገር ግን የት እንደነበርን ደግሞ የሚጠፋህ አይመስለኝም።
 • ክቡር ሚኒስትር እሱን እረዳለሁ ነገር ግን የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመከታተል የሚሆን የመረጃ አቅም አልነበረንም ለማለት እቸገራለሁ። 
 • ሥጋትህን ተረድቻለሁ። ውይይት ይደረግበታል። 
 • ክቡር ሚኒስትር ከአልሸባብ ጋር ተያይዞ መነሳት ያለበት ሌላም ጉዳይ አለ?
 • ምንድነው?
 • አልሸባብ ወረራ ፈጽሞብን ሳለ እንዲሁም አልሸባብ የሁላችንም የቀጣናው አገሮች ጠላት ሆኖ ሳለ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ግን እስካሁን በእኛ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አላወገዙም። 
 • እሱ እንኳን ብዙ የሚያሳስበን አይደለም።
 • እንዴት አያሳስብም ክቡር ሚኒስትር? አልሸባብ ከዚያው አገር እየተነሳ አይደለም እንዴ ጥቃት የሚሰነዝርብን?
 • ቢሆንም ለምን አላወገዙም ብለን መጨነቅ የለብንም፣ አሳሳቢ አይደለም።
 • ኩቡር ሚኒስትር እንዴት አያሳስብም? 
 • ምን ያሳስበናል?
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ቡድን ካላረፈ የሚቃጣብንን አደጋ ለመቀልበስ የገባበት መግባታችን አይቀርም። አሁን በማየው አዝማሚያ ግን አዲሱ የአገሪቱ መሪ ጀርባቸውን እየሰጡን ይመስለኛል። የሚቻለን አይመስለኝም። 
 • ለምን አይቻለንም?
 • ብንችል እንኳ የሁለት አገሮች ግጭት አድርገው በመሳል አገራችንን ለቀጣናው መረጋጋት ጠንቅ እንደሆነች አድርገው ይዘምቱብናል። ይህ ደግሞ ከባድ ዲፕሎማሲያዊ ኪሳራና ቅርቃር ውሰጥ እንዳይከተን እሠጋለሁ። በተጨማሪም
 • አይበቃህም…?
 • ክቡር ሚኒስትር ሌላም ችግር አለ። እየመጣ ያለውን ችግር ምሉዕ ሥዕል ልንመለከት ይገባል።
 • ምን የቀረ ነገር አለ? 
 • ክቡር ሚኒስትር አልሸባብ የፈጸመብንን ወረራ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማውገዝ ሲገባቸው ፕሬዚዳንቱ ግን ሌላ የኢትዮጵያ ባላንጣ የሆነችን አገር ሲጎበኙና በማይመለከታቸውን የህዳሴ ግድብ አጀንዳ አንስተው ሲወያዩ በይፋ በሚዲያ ጭምር ታይተዋል። ይህ ምን ማለት ነው? 
 • ቆይ… እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? 
 • ክቡር ሚኒስትር ጥያቄዎቼን አልጨረስኩም ነበር ግን አርሶ ጥያቄ ካለዎት ይጠይቁኝ!
 • እኔን ትወደኛለህ? 
 • እኔን ነው? 
 • አዎ። ትወደኛለህ?
 • “What love got to do with it?”
 • ምን አልክ?
 • መውደድን እዚህ ምን አመጣው ማለቴ ነው?
 • ግድ የለህም ጥያቄውን በቀጥታ መልስልኝ… ትወደኛለህ? 
 • ቆይ … አልወዶትም ብል ምን ይፈጠራል?
 • የመረጥከውን መመለስ ትችላለህ?
 • ክቡር ሚኒስትር … እወዶታለሁ ብልስ? 
 • መልስህን አሳውቀንና የእኔን ምላሽ ትሰማለህ። ደግም ልጠይቅህ… ትወደኛለህ?
 • እንደራሴ ባይሆንም እወዶታለሁ! 
 • ከወደድከኝ አሁን የምነግርህን ሰማኝ።
 • እየሰማሁ ነው።
 • ማንም ሊፍጨረጨር ይችላል ነገር ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ስለ መፍረስ አልጠየኩም? ነገር ግን ደግሞ አልሸባብ ወረራ ፈጽሞብናል።
 • እመነኝ። ኢትዮጵያ አትፈርስም!
 • ምን አገናኘው ክቡር ሚኒስትር?
 • ሥጋትህ ስለ ኢትዮጵያ አይደል?
 • አዎ።
 • እመነኝ ኢትዮጵያ አትፈርስም!
 • እንዴት ያለ ነገር ነው…?
 • የሌሎቻችሁንም መልስ ማወቅ እፈልጋለሁ። ትወዱኛላችሁ? 
 • አዎዎዎዎ…!
 • እንደዚያ ከሆነ የዛሬ ውይይታችን በዚሁ ቢጠናቀቅስ? 
 • ይሻላል ይጠናቀቅ… ይጠናቀቅ…
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር? እኔ ባነሳሁት ነጥብ ላይ ውይይት ይደረግበታል ብለው ነበር እኮ?
 • የቱ ጉዳይ?
 • በጥያቄ መልክ ያቀርብኳቸው ሥጋቶች?
 • ኮሚቴው በአብላጫ ድምፅ ከወሰነ ምንም ማድረግ አልችልም።
 • ኮሚቴው እኔ ባነሳሁት ነጥብ ላይ አልወሰነም።
 • ተናገረ እኮ አልሰማህም?
 • አልሰማሁም ምን ወሰነ? 
 • እንወድዎታለን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ሳምንት ያክል የፓርቲ ስብሰባ ላይ ቆይተው አመሻሹ ላይ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ባለቤታቸው በአግራሞት ተቀብለው ስለቆይታቸው ይጠይቋቸው ጀመር]

እኔ እምልክ...? ውይ... ውይ... በመጀመሪያ እንኳን በሰላም መጣህ፡፡ እሺ ...ምን ልትጠይቂኝ ነበር? ይህን ያህል ጊዜ የቆያችሁት ለስብሰባ ነው? ስብሰባ ብቻ አይደለም። ከስብሰባ ውጪ ምን ነበር? በተለያዩ መሪ ሐሳቦች የተዘጋጁ ሥልጠናዎችን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የፓርቲያቸውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ አጠናቀው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ቢሯቸው ውስጥ አማካሪያቸው አንድ ጽሑፍ በተመስጦ እያነበበ አገኙት]

ምንድነው እንደዚህ መስጦ የያዘህ ጉዳይ? መጡ እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ እያነበብኩ ነው፡፡ ግን እኮ ፊትህ ላይ የመገረም ስሜት ይነበባል፡፡ አዎ፣ መግለጫው ላይ...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን ሞባይል ስልካቸውን ተመለከቱ፣ የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ መሆናቸውን ሲያውቁ ስልኩን አነሱት]

ሃሎ... ጤና ይስልጥኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ተደራዳሪ... የጥረትዎን ፍሬ በማየትዎ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ እንኳን አብሮ ደስ አለን፣ ምን ልታዘዝ ታዲያ? የውኃ ሙሌቱንና አጠቃላይ የግድቡን የግንባታ ሁኔታ...