የሳውዝ ኦሞ ቴአትር ካምፓኒ ከለንደን ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ኦሬንታልና አፍሪካን ስተዲስ፣ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጋር በተመባበር በሙርሲዎች የተሠራ ቴአትር ለዕይታ አብቅቷል፡፡ በሙሪሲዎችና በሙርሲ ቋንቋ የተሠራው ቴአትር እሑድ ሐምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የታየ ሲሆን፣ ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ በብሔራዊ ቴአትር ለዕይታ ይበቃል፡፡ ሙዚቃዊ ቴአትሩ የሙርሲ የዕርቅ፣ የአመጋገብና ሌሎች ባህሎችን የሚያስተዋውቅ ነው፡፡
(መስፍን ሰለሞን)