Saturday, October 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ፍሬከናፍር‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ፈፅሞ ሊጣስ የማይችል ቀይ መስመር ነው››

  ‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ፈፅሞ ሊጣስ የማይችል ቀይ መስመር ነው››

  ቀን:

  ታዋቂው የሶማሊያ ኢማም፣ መምህር፣ የማኅበራዊ፣ የባህልና የፖለቲካ ተንታኝ ሼክ አብዲ ሂርሲ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ በግብፅ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው ካጋሩት የተወሰደ፡፡ ሼክ አብዲ ሂርሲ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትና አስተዳደር ላይ አሳሪ የሆነ ስምምነት መደረግ እንዳለበት መስማማታቸውን በግብፅ ሚዲያዎች መዘገቡን በተመለከተ፣ ‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ፈፅሞ ሊጣስ የማይችል ቀይ መስመር ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ ዘገባውን በግልጽ በመቃወም ሶማሊያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ወገናዊነት እንደሌላት ተዓማኒነት ያለው መግለጫ መስጠት አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት የግብፅና የሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች ሰሞኑን ካይሮ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ነው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img