Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለመንገድ ጥገና የሚውሉ ማሽነሪዎችን ለመግዛት የ360 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተደረገ

ለመንገድ ጥገና የሚውሉ ማሽነሪዎችን ለመግዛት የ360 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተደረገ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጃፓኑ ፊቸርበድ ኢንተርናሽናል ሊሚትድ ኩባንያ ጋር የ360 ሚሊዮን ብር ስምምነት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የገንዘብ ድጋፍ በኩል የተመቻቸው የመንገድ ጥገና ማሽነሪዎች ግዥ ስምምነትን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሞገስ ጥበቡ (ኢንጂነር) ከጃፓኑ ፊቸርበድ ኢንተርናሽል ሊሚትድ ኩባንያ ተወካይ አያሚናካዋ ጋር በበይነ መረብ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱም ባደረጉበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የመንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሞገስ ጥበቡ (ኢንጂነር) እንደገለጹት፣ በባለሥልጣኑ በኩል የሚደረግን የመንገድ ጥገና አቅም ለማሳደግ ስምምነቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

የተደረገው ስምምነት ከመንገድ መሠረተ ልማት ዕድገት ጎን ለጎን በከተማዋ በየዓመቱ የሚኖረው ወቅታዊና ተከታታይ የመንገድ ጥገና እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይኼም የባለሥልጣኑን የመንገድ ሀብት ጥገና አቅም በ25 በመቶ ያሳድገዋል ብለዋል፡፡

በግዥ ውል ስምምነቱ መሠረትም የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን 81 ማሽነሪዎችን ከጃፓን መንግሥት በግዥ እንደሚያገኝና የማሽነሪዎች ግዥ የጨረታ ሒደት በሦስት ሎት ተከፍሎ የሚከናወን እንደሆነ ሞገስ (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሠረት በሎት አንድና ሁለት ላይ የተዘረዘሩት 81 ማሽነሪዎች ግዥ በስምምነቱ መሠረት የሚከናወን መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያና የጃፓን ግንኙነት ከ90 ዓመት በላይ የቆየና ወሳኝነት ያለው መሆኑን በትምህርት በቴክሎጂ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ድጋፍ ማበረታታት እንደሚገባ ደግሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር የሆኑት ታካቢ ኦቶ፣ ኢትዮጵያ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ጋር ያላት ትስስር አዲስ አበባ መንገዶች እንደተቋም ሲዋቀር ጀምሮ መሆኑንና እ.ኤ.አ. በ1996 የተለያዩ የማሽነሪና የተሽከርካሪ ድጋፎች ተደርገው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2015 እስከ 2018 ድረስ መንገድ ጥገና አቅም ማሳደጊያ ፕሮጀክት ሲተገበር የቆየ ሲሆን፣ ይህም የመንገድ ጥገናን ውጤታማ በሆነ መንገደ ለማከናወን ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም የጃፓን መንግሥት ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለሌሎች ልማቶች የሚውሉ ድጋፎችን ማድረጉ ይታወቃል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...