- ድርድርን በሚመለከት የአሜሪካ መንግስት አቋም እንደማይዝ ተገለጸ
- በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች 488 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ተደረገ
መንግስት በወር ሁለት ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል እንዲያስገባ የተፈቀደለት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ)፣ ወደ ክልሉ ለመላክ የገዛውን ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ዩኤስኤድ በወር ሁለት ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል እንዲያስገባ የፈቀደው ባለፈው ወር ሲሆን ድርጅቱ ነዳጁን የሚያስገባው ከታክስ ነጻ መሆኑን ገልጿል፡፡
ድርጅቱ የገዛውን ነዳጅ የጫኑ የመጀመሪያዎቹ ተሽከርካሪዎች ትናንት ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓም ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን አስታውቀዋል፡፡ ትሬሲ አክለውም፣ መኪኖቹ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ይሄዳሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ጉዳይ አስፈጻሚዋ ይሄንን የገለጹት ዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል የ488 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ ባደረገበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው 488 ሚሊዮን ዶላር ድርቅ ባለባቸው አከባቢዎች የሚገኙ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለመድረስ አቅዷል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ወስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 8.1 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ድርጅቱ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስታውቋል፡፡
በመግለጫው ላይ፣ የፌደራል መንግስትና ህወሃት ሊያደርጉ ስላሰቡት ድርድር የአሜሪካ መንግስት አቋም ምን እንደሆነና የአሜሪካ መንግስት በማን ጥላ ስር የሚደረግ ድርድርን እንደሚደግፍ ለአምባሳደር ትሬሲ ጥያቄ ቀርቧል፡፡
- Advertisement -ጉዳይ አስፈጻሚዋ የአሜሪካ መንግስት ሁለቱ አካላት ወደ ድርድር ለመግባት መወሰናቸውን በመልካም እንደሚያየውና ለአፍሪካ ህብረትም ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ድርድሩ እንዴት፣ መቼና በምን አይነት ሁኔታ ይካሄድ የሚለው ላይ አቋም እንደማይዝ አስታውቀዋል፡፡ ትሬሲ ይሄንን ሲያስረዱም፣ “ንግግሩ እንዴት ይሂድና መቼ ይደረግ የሚሉ ዝርዝሮች የተደራዳሪዎቹ ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ያ እንዴት መከናወን አለበት፣ ማን ምን ያድርግ የሚለው ላይ አቋም አንይዝም” በማለት ተናግረዋል፡፡
- Advertisement -
ለትግራይ የተገዛው ነዳጅ ከጅቡቲ መግባት ጀመረ
- Advertisement -