የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2014 ሂሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 27.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓም አስታወቀ።
ትርፉ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ሂሳብ ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ43 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።
ባንኩ ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ስብሰባ እንደገለጸው፣ ሀብቱ 1.7ትሪሊዮን ብር ደርሷል።ጠቅላላ ተቀማጭ ገነዘብም 890 ቢሊዮን ብር መድረሱን የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ አቢ ሳኖ ተናግረዋል።