የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓም ከተባበሩት መንግስታት፣ከአውሮፓ ኅብረት፣ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛና አምባሳደር፣ ከአሜሪካ፣ጣሊያን፣ፈረንሳይ፣እንግሊዝና ጀርመን አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪው ሬድዋን ሁሴን(አምባሳደር)ና የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዴዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ተሳትፈዋል።
ባለስልጣናቱ ባደረጉት ውይይት፣ የኢትዮጵያ መንግስት በማንኛውም ጊዜና በማንኛውም ቦታ ውይይቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መጀመር እንዳለበትና ለሱም ፈቃደኛ መሆኑን ማሳወቃቸውን ሬድዋን(አምባሳደር) በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል።
አምባሳደሮቹና ልዩ መልዕክተኛው ወደ መቀሌ መሄድ እንዲችሉ መፈቀዱንም አክለዋል።