Sunday, December 10, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ንግድ ባንክ በዲጂታል ባንኪንግ ከ1.2 ትሪሊዮን ብር በላይ ማዘዋወሩ ተሰማ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቅርንጫፎቹ ውጪ በዲጂታል የባንኪንግ አገልግሎት ብቻ፣ ከ1.2 ትሪሊዮን ብር በላይ ማንቀሳቀስ መቻሉ ተገለጸ፡፡

ባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱን ከዓመት ዓመት እያሳደገ የተጠቃሚዎችን ቁጥር በመጨመር፣ በበጀት ዓመቱ ብቻ የዲጂታል ባንኪንግ በመጠቀም የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን መዘዋወሩ ታውቋል፡፡

የ2014 የሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ የንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በተከታታይ በተደረጉ ሥራዎች 35 በመቶ የሚሆኑ ደንበኞች እንቅስቃሴዎች ከቅርንጫፍ ውጪ ባሉ አማራጭ የዲጂታል ባንኪንግ የተከናወኑ ናቸው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሞባይልና የኢንተርኔት ባንኪንግ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑንና አገልግሎቱም እየተሻሻለ ነው ያሉት አቶ አቤ፣ በ2014 የሒሳብ ዓመት ብቻ ተጨማሪ 2.3 ሚሊዮን የካርድ፣ 3.9 ሚሊዮን የሞባይል ባንኪንግ፣ 35 ሺሕ የኢንተርኔት ባንኪንግና 3.9 ሚሊዮን የሲቢኢ ብር ደንበኞች ማፍራት መቻሉን ገልጸዋል፡፡  

በዚህም የባንኩ አጠቃላይ የኤቲኤም ተጠቃሚዎች ቁጥር 7.73 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን፣ ከዚህም በተጨማሪ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር 5.94 ሚሊዮን መድረሱን ያስታወቁት አቶ አቤ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር 39 ሺሕ መድረሱንና የሲቢኢ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ደግሞ 5.38 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለማበራከት አሁንም ተጨማሪ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አክለዋል፡፡

አማራጭ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትን ለመስጠት ባንኩ አስፈላጊ መሠረት ልማቶችን እየሠራና እያሰፋ የሚገኝ መሆኑን ተገልጾ፣ እስከ 2014 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ድረስ የኤቲኤም ማሽኖችን ቁጥር 2,766 ማድረሱን ተመላክቷል፡፡  

የፖስ ማሽኖቹ ቁጥር ደግሞ 4,861 መድረሳቸውን የባንኩ ዓመታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ንግድ ባንክ በ2014 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የቆጣቢ ደንበኞቹ ቁጥር ከ35 ሚሊዮን በላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በመላ አገሪቱ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 1,824 ያደረሰው ንግድ ባንክ ከ70 ሺሕ በላይ ሠራተኞች እንዳሉት ይታወቃል፡፡

ዘንድሮ ባንኩ ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት 27.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች