Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢንቨስትመንት የሚሻው የተፈጥሮ ሀብት

ኢንቨስትመንት የሚሻው የተፈጥሮ ሀብት

ቀን:

በአገርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የደን ሀብት ለተጨማሪ ገቢ ማስገኛ፣ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለሥራ ፈጠራና ለምግብ ዋስትና ዕውን መሆን የሚኖራቸው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍተኛ ቢሆንም፣ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎች በቅንጅት፣ በጋራና በአግባቡ ካልተከናወኑ በረሃማነት ከመስፋፋቱ ባሻገር በብዝኃ ሕይወት ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡

ይህም በግብርና፣ በኢነርጂና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ምርትና ምርታማነት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ ከአፍሪካ አምስተኛ፣ ከዓለም 25ኛ ደረጃ ላይ ብትገኝም ከሀብቱ እምብዛም ተጠቃሚ አይደለችም፡፡ ለዚህም ኢንቨስትመንትን ከተፈጥሮ ሀብት ጋር አስተሳስሮ አለመሥራት እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

ወርልድ ቪዥን በኢንቫይሮመንት፣ በውኃና በዋሽ ፕሮግራሞች ዙሪያ ለሁለት ቀናት ያካሄደው ዓውደ ጥናት ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጀመረበት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የደን ልማት ኃላፊ አቶ ከበደ ይማም እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ ከ54 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሆነው ተራቁቷል፡፡

ከተራቆተው መሬት ውስጥም 11 ሚሊዮን ሔክታር ያህሉ አስቸኳይ ክብካቤ እንደሚያስፈልገው ገልጸው፣ ይህ ካልሆነ ወደ በረሃማነት እንደሚሸጋገር፣ ይህም እንደተጠበቀ ሆኖ የደን መመናመንን፣ የመሬት መራቆትንና በውኃ ሀብት ዘላቂ ልማት ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ሁኔታ ለመቀየር የሚያስችል በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሆነ የገለጹት አቶ ከበደ፣ በመከናወን ላይ ካሉት ተግባራት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በመካሄድ ላይ ያለው የ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› ተነሳሽነት አንዱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከአረንጓዴ አሻራ ዋነኛዎቹ ዓላማዎች መካከል የደን ማኔጅመንት፣ የውኃና ኢነርጂ ልማት፣ የግብርና ምርት፣ የኢንዱስትሪ መስፋፋት፣ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እንዲሁም በቀጣይ አሥር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ያላትና ከበካይ ካርቦን ነፃ የሆነች አገር እንድትሆን ማስቻል የሚሉት እንደሚገኙበትም አክለዋል፡፡  

‹‹የተፈጥሮ ሀብት ላይ ኢንቨስት ሳይደረግ በውኃ ላይ ብቻ ኢንቨስት ቢደረግ የንፁህ መጠጥ ውኃ የሚኖረው ተደራሽነት አናሳ ይሆናል፤›› ያሉት ደግሞ የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የላይቭሊሁድ ፕሮግራም ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ወንዳፈራሁ ናቸው፡፡

እንደ ኃላፊው፣ በአንድም በሌላም ለውኃ ያለን ተደራሽነት ከተፈጥሮ ሀብት ማኔጅመንት ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ዋሽ (ዋተር፣ ሳኒቴሽን ኤንድ ሃይጅን) እና ኢንቫይሮመንት ዘርፎች መቀናጀት ተስኗቸው አንደኛው ዘርፍ በሌላው ዘርፍ እየተጎዳ እስከዛሬ ድረስ እንደዘለቁ ኃላፊው አመልክተው፣ ዘርፎቹ ከፖሊሲ ጀምሮ በደንብ እየተናበቡ መሥራት ካልቻሉ የንፁህ መጠጥ ውኃ ተደራሽነት እያነሰ እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡

‹‹ቀደም ባሉት ዓመታት 30 እና 40 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ተቆፍሮ ለመጠጥ የሚውል ውኃ ይወጣ ነበር፡፡ አሁን ግን ውኃ ለማግኘት እስከ 250 ሜትር ድረስ የሚዘልቅ ጥልቅ ጉድጓድ መቆፈር ግድ እየሆነ መጥቷል፡፡ ለዚህ አንድ ምክንያት ነው ተብሎ የሚታሰበውና በሳይንሳዊ መረጃዎችም የተደገፈው በተፈጥሮ ሀብት ላይ በቂ ሥራ አለመሠራቱ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የመጠጥ ውኃ የሚገኝበት ዋናው ምንጩ የከርሰ ምድር ውኃ መሆኑን ወርልድ ቪዥን በመገንዘቡ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች 250 ጥልቅ ጉድጓዶችን በመቆፈር ላይ መሆኑን፣ ይህም ሆኖ ግን ድሮ በቅርብ ቁፋሮ ይገኝ የነበረው ውኃ አሁን እየራቀና በዚያውም ልክ ተደራሽነቱም እየቀነሰ እንደመጣ አመልክተዋል፡፡

የግንባታዎች መስፋፋት ለምንጮች መድረቅ ምክንያት ናቸው ይባላል፡፡ እርስዎ በዚህ ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድነው? ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹ውኃ ወደ ከርሰ ምድር በሚገቡባቸው ቦታዎች ላይ ማንኛውም ዓይነት ግንባታ ማካሄድ አይቻልም፡፡ በሠለጠነው ዓለም የሚታየው ይህ ዓይነቱ አካሄድ ነው፡፡ በእኛ አገር ግን የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ቀርቶ ጥናትም ያለ አይመስለኝም፡፡ ውኃ ወደ ከርሰ ምድር በሚሠርግባቸው ቦታዎች ላይ ሕንፃ ከተገነባ በዝናብ መልክ የሚመጣው ውኃ ወደ ከርሰ ምድር ከመሥረግ ይልቅ ወደ ወንዝ ይወርዳል፤›› ብለዋል፡፡ 

በኔክሰስ ሆቴል በተከናወነው በዚሁ ዓውደ ጥናት ላይ ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኘው የውኃ ሀብት ከተጠበቀው በላይና በአግባቡ ባለመጠቀም እንዲሁም በብክለት የተነሳ ሥጋት ላይ ወድቋል፡፡

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በአገሪቱ ቀጣይና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት እንዲቻል ከመንግሥት፣ ከምርምርና አካዴሚክ ተቋማት፣ ከቴክኒካል ልማት ተዋናዮች፣ ከአካባቢው ማኅበረሰቦችና የእምነት መሪዎች ጋር በቅንጅትና በትብብር እየሠራ መሆኑን፣ ዓምና ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን የውኃና የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦ ማበርከቱን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...