Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ተፅዕኖ እየደረሰበት ነው መባሉን ኮሚሽነሮቹ ውድቅ አደረጉ

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ተፅዕኖ እየደረሰበት ነው መባሉን ኮሚሽነሮቹ ውድቅ አደረጉ

ቀን:

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ነፃነትና ገለልተኝነት ተፅዕኖ እየደረሰበት ነው መባሉን ኮሚሽነሮቹ ውድቅ አደረጉ፡፡ የኮሚሽኑ የሦስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ለውይይት በቀረበበት ወቅት፣ በኮሚሽኑ ነፃነትና ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡፡ ስለዚሁ ምላሽ የሰጡት ኮሚሽነሮቹ፣ ኮሚሽናቸው ነፃና ገለልተኛ በሆነ መንገድ እንደሚንቀሳቀስ አስታውቀዋል፡፡

ቅዳሜ ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ለተሳታፊዎች ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ በዕለቱ ተሳታፊ ከሆኑ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ፖለቲከኞች፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችና የሚዲያ ሰዎች በረቂቁ ላይ ግብዓት የተሰበሰበ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችም ለኮሚሽኑ ቀርበዋል፡፡

ከእነዚህ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል ደግሞ ኮሚሽኑ በገለልተኝነትና በነፃነት መሥራት የሚያስችል ሁኔታ ያለው ስለመሆኑ በዋናነት ተነስቷል፡፡ ከ11 የምክክር ኮሚሽነሮች አንዱ የሆኑት አቶ መላኩ ወልደማርያም ምላሽ ሲሰጡ፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ማንንም የማይፈሩና በምንም ነገር የማይደለሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹ስለኮሚሽኑ ገለልተኝነትና ነፃነት በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ ስለኮሚሽኑ ሲነገር ግን በቀጥታ ኮሚሽነሮችን ማለት ነው፡፡ ኮሚሽኑን ሕይወት እንዲኖረው የምናደርገው እኛ እንጂ ኮሚሽኑ ግዑዝ ነው፡፡ ባለፉት አምስት ወራት በዚህ ኮሚሽን ቆይታዬ ያየሁት ግን ፍፁም አገራቸውን የሚወዱ፣ ፍፁም ቅን የሆኑ፣ ዝቅ ብለው ሁሉንም ማገልገል የሚፈልጉ ልበ ሰፊ ሰዎች መሰብሰባችንን ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ከምንም በላይ ኮሚሽነሮች ፈጣሪን ብቻ እንደሚፈሩ የጠቀሱት አቶ መላኩ ‹‹ሰው ይከበራል፣ ሕዝብ ይከበራል፣ መንግሥትም ይከበራል፡፡ የሚፈራ ግን ፈጣሪ ብቻ ነው፤›› በማለት፣ ሁሉም የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ለእውነት እንደሚቆሙ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ቃለ መሃላ በመፈጸማችን ብቻ ሳይሆን ለእውነትና ለልጆቻችን ክብር እንቆማለን፡፡ በጥቅም አንደለልም፣ በሥልጣንም አንደለልም፣ ፈጣሪ ይመሥገን የበሰልን ሰዎች ነን፤›› በማለት አቶ መላኩ አክለዋል፡፡

ስለኮሚሽኑ መሠረታዊ ሥልጣንና የሥራ ኃላፊነት ያብራሩት ዋና ኮሚሽነሩ መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) በበኩላቸው፣ በአዋጅ ከተሰጠው ሥራና ኃላፊነት የተለየ ውጤት እንዳይጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ የኮሚሽኑን ኃላፊነት መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ሥራችን ሕዝቡ ጋ ወርዶ አጀንዳን ማምጣት ነው፡፡ ሕዝቡ የክልልም ሆነ የፌዴራል ሕገ መንግሥት ይሻሻል ወይ ይቀየር የሚል ከሆነ ሥራችን በየደረጃው እንዲመለስ ማቅረብ ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኮሚሽናችን አጀንዳ ራሱ ቀርፆ ሕዝቡን ተወያይ የማለት የአዋጅ ሥልጣን አልተሰጠውም፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ተዓማኒነትና ገለልተኝነትን በተመለከተ፣ ‹‹በራችን ክፍት ነውና ሁላችሁም ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ፤›› ያሉት መስፍን (ፕሮፌሰር)፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ በአገራዊ ምክክሩ ጉልህ ድርሻ ያላቸው አካላት በሙሉ ኮሚሽኑን በቅርበት በመከታተልና በጋራ በመሥራት የራሳቸውን ብይን እንዲሰጡ ነው የጠየቁት፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...