Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየጠበቆች አስተዳደር የቦርድ አባላት ሹመት የእኩልነት መርህን የጣሰ ነው ተባለ

የጠበቆች አስተዳደር የቦርድ አባላት ሹመት የእኩልነት መርህን የጣሰ ነው ተባለ

ቀን:

ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.መ. በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አፅዳቂነት ወደ ሥራ የገባው የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ሹመት፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ያላካተተ፣ የሥርዓተ ፆታ ሚዛን የሳተ፣ የአካታችነትና የእኩልነት መርህን የጣሰ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር አስታውቋል፡፡

በፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/13 አንቀጽ (69) ድንጋጌ መሠረት የተደረገው ሹመት፣ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚጋፋ፣ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የእኩልነት መብትን የሚጥስና የሴቶችን 50 በመቶ ውክልና የሚጋፋ መሆኑን፣ ማኅበሩ ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሌንሳ በየነ እንደተናገሩት፣ ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የፍትሕ ሚኒስቴር በይፋዊ የፊት ገጹ ላይ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ አባላትን በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አማካይነት ማፅደቁንና በይፋ ሥራ መጀመራቸውን አሳውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይህም የሴት የሕግ ባለሙያዎች በራሳቸው የመወሰን መብትን የሚጋፋ፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 25 እና 35 ላይ በተደነገገው መሠረት የሴቶችና የወንዶች እኩልነትን የሚጥስና የሚጋፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሥርዓተ ፆታ ፖሊሲ መሠረት የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ወደ አመራርነት ማምጣት አስፈላጊ መሆኑ መደንገጉን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በዚህ መሠረት መሻሻል መታየቱን፣ ነገር ግን ጅማሮው በታሰበው ፍጥነት አለመጓዙን አስረድተዋል፡፡

ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መሆኑን፣ ለማሳያነትም የፌዴራል መንግሥትና የሕወሓት አደራዳሪ ቡድን ውስጥ የነበረው የፆታ ተሳትፎ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ማኅበሩ ከሌሎች መሰል ተቋማት ጋር በመሆን ድርጊቱን ማውገዙን አስታውሰው፣ ሴቶችን የኢትዮጵያን ከግማሽ በላይ ለሚሆኑ ኅብረተሰብ ክፍሎች ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ አለማድረግ ውጤት አልባ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

ማኅበሩ የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ አባላት 50 በመቶ ብቃት ያላቸው ሴቶችን እንዲሆኑ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም፣ በተደረገው ሹመት ላይ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የሴቶችን እኩልነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ ጽሕፈት ቤቱ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማኅበር፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በሴቶች ዙሪያ ለሚሠሩ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችና በዘርፉ ለሚሠሩ ዓለም አቀፍ ተቋማትን የቦርድ የአባላት ሹመትን በተመለከተ የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና የአካል ጉዳተኞች መብትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በድጋሚ እንዲታይ ማኅበሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳን ይርጋ በበኩላቸው፣ ከሰብዓዊ መብት መርሆች አንፃር፣ የጠበቆች አስተዳደር የቦርድ አባላት ምርጫ ትልቅ ክፍተቶች እንዳሉባቸውና በአስቸኳይ ሊታረም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሹመቱ መርህን የጣሰና ተገቢ ያልሆኑ ሒደቶች የተከተለ መሆኑን፣ ድርጊቱን የፈጸሙትም የተማሩ ምሁራን ስብስብ እንደሆኑ የገለጹት አቶ ዳን፣ የሴቶችና አካል ጉዳተኞችን የእኩልነት መብትን የጣሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የሥርዓተ ፆታን እኩልነት ማረጋገጥ የሚገባቸው ማንም ሳይነግራቸው እንደሆነ፣ ሊያመጣ የሚችለውን ፖለቲካዊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ መዘንጋት እንደሌለባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሴቶች እኩልነትን ማረጋገጥና ወደ አመራርነት የማምጣት ሒደትን ወደኋላ የሚጎትት ተግባር መሆኑን የገለጹት አቶ ዳን፣ የቦርድ አባላት ምርጫ በድጋሚ መታየትና መስተካከል እንዳልበት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም እንዳስረዱት፣ በኢትዮጵያ በሙያቸው ትልቅ ቦታ የደረሱ ሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ጥያቄያቸው አግባብነት ያለው መሆኑን የገለጹት አቶ ያሬድ፣ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሠሩና በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ተቋማት በጠቅላላ ጥሪው መስተጋባትና መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

በፍሕ ሚኒስቴር ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የሴቶችን የማካተት ጥያቄዎች እንደነበሩ ጠቁመው፣ የማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ሴቶች በሥራ አስፈጻሚው መሾማቸውንና መሳተፋቸውን በቂ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ተናግረዋል

 ማኅበሩ በጥሪያቸው መሠረት ማስተካከያ ይደረጋል ብለው እንደሚጠብቁ፣ ነገር ግን ማስተካከያ ካልተደረገ ግፊትና ጫናው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ አካታችነትና እኩልነት ተጠይቆ የሚገኝ መብት መሆን እንደሌለበት፣ እንደ አገር ችግሩ መቀረፍ እንዳለበትም አክለዋል፡፡

በእያንዳንዱ ነገሮች የሴቶች ይካተቱ ጥያቄ መሠረት ውሳኔዎች መሰጠት እንደሌለባቸው የማኅበሩ አባል ሃና ኃይለ መለኮት ያስረዱት፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት በራሳቸው ተነሳሽነት ማድረግ እንደሚገባቸው ግዴታቸው ጭምር መሆኑን አስረድተዋል

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...