በባሌ ዞን ኦሮምያና ሱማሌ ክልሎችን በሚያዋስነው የጉራ ዳሞሌ ቀበሌ 8759 ዜጎች (1040 አባ ወራዎች) ተፈናቅለዋል፡፡ ከአንድ ወር በፊት ከመኖሪያ ቀዬአቸው የተፈናቀሉት ዜጎቹ፣ በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ ከሌ ጎልባ ቀበሌ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ግጭቱ እንደ ተከሰተ ከመኖሪያ ቀዬአቸው 70 ኪሎ ሜትር ርቀት የተጓዙት ተፈናቃዮዎቹ፣ መጠለያ ሥፍራ አግኝተው ሰብዓዊ ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
