Monday, December 4, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

 • ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል።
 • በጣም ጥሩ ዜና ነው።
 • በጣም እንጂ። የሚገርምዎት ነገር ክቡር ሚኒስትር …
 • እህ…
 • ምክራችንን ተቀብለው አርሶ አደሮቻችን በኩታ ገጠም ያለሙት የስንዴ ማሳ ከግዝፈቱ የተነሳ በአየር ካልሆነ ተጉዘው አይጨርሱትም።
 • ‹የስንዴ ምንቸት ግባ› ለማለት ተቃርበናል በለኛ፡፡
 • በመጪው ዓመት የሚሳካልን ይመስለኛል። ግን ክቡር ሚኒስትር …
 • ግን ብለህ እስካሁን ያወራኸውን ልታፈርሰው እንዳይሆን ብቻ?
 • አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ምንድነው?
 • አርሶ አደሮቻችን እንዲህ እየለፉ ቢሆንም በአመራሮቻችን በተለይም በታችኛው መዋቅራችን ላይ ቅሬታ አላቸው። 
 • ለምን?
 • ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ በሚተጉ አመራሮች ተንገላታን ነው የሚሉት።
 • እንዴት? አልገባኝም። 
 • አንዴ የዞን አመራሮች የሰንዴ ማሳ ሊጎበኙ መጥተዋል ተብለው አስጎብኙ ይባላሉ።
 • እሺ…
 • ደግሞ ከወረዳ መጥተዋል… ቀጥሎ ከቀበሌ ይባሉና ይጠራሉ፣ ያለማቋረጥ ሲያስጎበኙ ይወላሉ። 
 • እንዴት ያለ ነገር ነው…?
 • አርሶ አደሮቹ አስጎብኙ በመባላቸው አይደለም ቅር የተሰኙት ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ በምንድነው ቅር የተሰኙት? 
 • የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ ሌላ መሆኑን በማወቃቸው ነው።
 • እንዴት ….ዋነኛ ዓለማው ምንድነው?
 • አመራሮቹ የስንዴ ማሳ ለመጎብኘት ፊልድ ወጥተናል እያሉ የውሎ አበል ክፍያ ለመሰብሰብ እንደሚጎበኟቸው በማወቃቸው ነው ያዘኑት።
 • እንዲህ ሊሆን አይችልም፡፡
 • እንደዚያ ነው ክቡር ሚኒስትር። እኛም ቅሬታውን ከሰማን በኋላ ባደረግነው ማጣራት በየአካባቢው ለስንዴ ማሳ ጉብኝት ተብሎ ለአመራሮች የተከፈለው የውሎ አበል ወጪ አሰደንግጦናል። 
 • ምን ዓይነት ጉድ ነው ይኼ?
 • ቢሆንም ክቡር ሚኒስትር አርሶ አደራችንም የዋዛ አይምሰልዎት። 
 • እንዴት? 
 • ከበላይ አካል መፍትሔ እስኪመጣ ሳይጠብቅ በየአካባቢው መፍትሔ ያለውን የራሱን ዕርምጃ ወስዷል፡፡
 • ምን ዓይነት ዕርምጃ ወሰደ?
 • የስንዴ ማሳ ልጎብኝ እያለ የሚተመውን አመራር በጥያቄ አፋጧል። 
 • ምን ብሎ ነው ያፋጠጣቸው?
 • ከማፋጠጥ አልፎም ያቀረብኩት ጥያቄ ካልተመለሰ የስንዴ ማሳውን አላስጎበኝም እያለ ወደመጡበት እየመለሰ ነው።
 • አርሶ አደሩ ያቀረበው ጥያቄ ምንድነው?
 • ለእኔም ይከፈለኝ፡፡ 
 • ምን?
 • አበል! 
 • ታዲያ አመራሩ ምን አለ?
 • ለማወራረድ አይመችም። 

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሕዝብ መገለጽ አለበት ተብሎ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ኮሚቴው ባቀረበው ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ቢሆንም ነገሩ አልጣማቸውም]

 • ክቡር ሚኒስትር ሕዝቡ ተጨንቋል…
 • በምን ምክንያት?
 • ሚኒስትሩ ከሚዲያ በመጥፋታቸው ተጨንቋል። ኧረ እንደውም ነገሩ ከመጨነቅ ያልፋል!
 • እንዴት?
 • ምክንያቱም ሚኒስትሩ ከሚዲያ መጥፋታቸው ብቻ አይደለም እየተወራ ያለው። 
 • ሌላ ምን እየተወራ ነው?
 • ሚኒስትሩ አንድ ነገር ቢሆኑ ነው የጠፉት እያለ ነው ሕዝቡ።
 • ሕዝቡ …ሕዝቡ የምትለው ነገር አይዋጥልኝም። 
 • እንዴ ክቡር ሚኒስትር …ሕዝቡ መጨነቁን ዓይቼ እንጂ እኔ ከየት አመጣዋለሁ?
 • ሕዝቡ …አሁንም ሕዝቡ… ማነው ሕዝቡ? 
 • ክቡር ሚኒስትር…
 • ቆይ ሕዝቡ ተጨንቋል የምትለው የት አይተኸው ነው?
 • ማኅበራዊ ሚዲያ አይከታተሉም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • አየህ …የፈራሁት ይኼንን ነበር! ጭንቀት የምትለው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚራገብ ወሬን እንደሆነ ጠርጥሬ ነበር።
 • ክቡር ሚኒስትር ማኅበራዊ ሚዲያን ባይንቁ ጥሩ ነው።
 • ለምን አልንቅም?
 • ምክንያቱም የዘመኑ የመረጃ ገበያ ማኅበራዊ ሚዲያ ነው። መንግሥትም ይህንን አምኖ እየተጠቀመበት ነው። ስማቸውን ቀይረው ቢሆንም ሁሉም ሚኒስትሮች ማኅበራዊ ሚዲያን ይጠቀማሉ።
 • እንተም በሌላ ስም ትጠቀማለህ እያልከኝ ነው?
 • እንደዚያ አላልኩም። 
 • እና ምን እያልክ ነው?
 • ቢጠቀሙ ግን ጥሩ ነው እያልኩ ነው።
 • ምን ጥሩ ነገር አለው?
 • ቢያንስ የሕዝቡን ትርታ ያደምጡበታል። ማስተላለፍ የሚፈልጉት ነገር ያለ እንደሆነም በቀላሉ ሚሊዮኖች ጋር ማድረስ ይችላሉ።
 • የሕዝቡን ትርታ ለማዳመጥ እንኳን ጠቃሚ ነው። እኔም አልፎ አልፎ እመለከታለሁ አንዳንዴም እጠቀማለሁ።
 • ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አሉ? …እንዴት አይቼዎት አላውቅም?
 • የለሁም ግን አልፎ አያለሁ፡፡ 
 • እንዴት አድርገው?
 • እሱን ተወውና ወደ ዋና ገዳያችን ብንመለስ?
 • ጥሩ ክቡር ሚኒስትር። እኔ እያልኩ ያለሁት ሕዝቡ ሚኒስትሩ ለምን ጠፉ ብሎ ተጨንቋል ነው። ባይጨነቅ እንኳ እኛ የማሳወቅ ግዴታ አለብን። 
 • የምን ግዴታ አለብን?
 • ምክንያቱም ሕዝቡ ሚኒስትሩ ያሉበትን ሁኔታ የማወቅ መብት አለው። የማወቅ መብት አለው ማለት ደግሞ እኛ የማሳወቅ ግዴታ አለብን ማለት ነው። በተጨማሪም …
 • በተጨማሪ ምን?
 • እንደዚህ ያሉ ነገሮች ፈጣን መረጃ ካልተሰጠባቸው ሕዝቡን ለተሳሳቱ መላምቶች ይዳርጋል። ጠላቶቻችን ደግሞ ክፍተቱን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። 
 • ስለዚህ ምን መደረግ አለበት ነው የምትለው?
 • ሚኒስትሩ በመደበኛ ሥራቸው ላይ እንደሚገኙና በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚነዛው አሉባልታ እንደሆነ የሚገልጽ መግለጫ ብናወጣ ጥሩ ነው። 
 • ግን ይህንን እኛ ማድረግ አንችልም።
 • ለምን?
 • መደበኛ ሥራቸው ላይ ባይሆኑስ? እውነት ለመናገር እኔም አግኝቻቸው አላውቅም። 
 • ለምን በቀጥታ ደውለው አይጠይቋቸውም።
 • ምን?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር። ደውለው ሥጋታችን ያስረዷቸውና መደበኛ ሥራቸው ላይ መሆናቸው በዘዴ በሚዲያ ይተላለፍ?
 • እንደዚያ ማድረግ አልችልም።
 • ለምን ክቡር ሚኒስትር? ለምን?
 • ባለፈው ፓርላማውን ሲቆጡ ያየ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ዳግመኛ አያቀርብም። 
 • ፓርላማውን ተቆጥተዋል እንዴ? 
 • አላየህም እንዴ? 
 • አላየሁም። ምን ብለው ተቆጡ?
 • ፓርላማው ባልሰጠኝ በጀት ላይ ሊጠይቀኝ አይችልም ብለው ነዋ።
 • እንደዚህ ብለው ተቆጥተዋል? 
 • ታዲያ?!
 • አልሰማሁም። እንደዚያ ከሆነማ
 • እ….
 • ይቅርብን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...

በሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ የታየው ተሞክሮ በሌሎች ምርቶች ላይም ይስፋፋ!

ሰሞኑን በኢትዮጵም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ግዙፍ ስለመሆኑ የተነገረለትን የለሚ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን? ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት? ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ...

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የካቢኔና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባል የሆኑ ከፍተኛ አመራር የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረግህ፣ ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[ጉባዔው በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ክቡር ሚኒስትሩን ለመጠየቅና ምላሽና ማብራሪያቸውን ለማድመጥ ተሰብስቧል። የጉባዔው አባላትም ማብራሪያ የሚሹ ጥያቄዎቻቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር፣ ይህ ጉባዔ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በመካከላችን ስለተገኙ አመሰግናለሁ። ክቡር ሚኒስትር፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የብሪክስ አባል እንድትሆን የሰጡት በሳል አመራር የሚደነቅ ነው። አገራችን...