Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ኮንትራታቸው እንዲታደስ ጥያቄ አቀረቡ

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ኮንትራታቸው እንዲታደስ ጥያቄ አቀረቡ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ኮንትራታቸው እንዲታደስ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ከቃል ውይይት ባለፈ በፌዴሬሽኑ በኩል የተረጋገጠ ምላሽ እንዳላገኙ ተናገሩ፡፡ ዋና አሠልጣኙ የኮንትራቱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አሁን ላይ ግን ትኩረት ማድረግ የሚፈልጉት ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ላለባቸው የመጨረሻ ጨዋታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ስለ ኮንትራታቸው ጉዳይ የተናገሩት፣ ቡድናቸው ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር በታንዛኒያ ያደረገውን የደርሶ መልስ ጨዋታ አስመልክቶ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

  ከተለያዩ ክለቦች ጥያቄ ቀርቦላቸው እንደነበር የተናሩት አሠልጣኝ ውበቱ፣ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር ከኮንትራታቸው ጋር በተገናኘ ምንም የቋጩት ነገር ባለመኖሩ ጥያቄውን ለመቀበል አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ይሁንና የክለቦቹ ጥያቄ አሁን ባለው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ያበቃለት ስለመሆኑ ጭምር ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

  ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የአሠልጣኝ ውበቱን ኮንትራት በተመለከተ ቀደም ሲል እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሆነ ነው፡፡

  በዚህ ጉዳይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃለፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን፣ ኮንትራቱን ጨምሮ አሠልጣኝ ውበቱ አንዳንድ ሊሟሉላቸው የሚገቡ ጥቅማ ጥቅሞችን ያካተተ ጥያቄ እንዳቀረቡ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ይህንኑ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ከአሠልጣኙ ጋር ውይይቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ጭምር ነው ኃላፊው ያስረዱት፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...