Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልአራተኛው ሆሔ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ሊካሄድ ነው

አራተኛው ሆሔ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ሊካሄድ ነው

ቀን:

ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው ሆሔ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት የግል ታሪክና አጭር የልብ ወለድ ዘርፎችን በመጨመር ጳጉሜን 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሆሔ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ‹‹መጽሐፍት›› ለዕውቀት ዳበራ! ለጥበብ ጎታ!  በሚል መሪ ቃል፣ በአሥር የሥነ ጽሑፍ ዘርፍ እንደሚካሄድ አቶ ኤፍሬም ብርሃኑ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት አዳዲስ ዘርፎችን መጨመራቸውን የተናገሩት አቶ ኤፍሬም፣ ግለ ታሪክና አጭር ልብ ወለድ መጽሐፍት መካተታቸውን ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

የልጆች መጽሐፍት፣ ግጥም፣ ረዥም ልብ ወለድ፣ ጥናትና ምርምር ጨምሮ በስድስት የመጽሐፍት ዘርፎችና የሕይወት ዘመን የሥነ ጽሑፍ ባለውለታና በንባብ እንዲዳብር አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት ጋር በአጠቃላይ በአሥር ዘርፎች ሽልማት እንደሚሰጡ አክለዋል፡፡

ሐሸማል (በማዕበል ፈጠነ)፣ ምሳሌ (በእንዳለጌታ ከበደ)፣ ስለትናንሽ አለላዎች (በዮናስ አጋ)፣ ታለ፣ በእውነት ስም (በዓለምአየሁ ገላጋይ)፣ አብራክ (በሙሉጌታ አረጋዊ) በረዥም ልብ ወለድ ዘርፍ የታጩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ኤፍሬም እንደተናገሩት፣ የሰባቶች ጋጋታ (በተስፋዬ ገብረ ማርያም)፣ አዕምሮ የተረት መጽሐፍት፣ ብስክሌቱና ሌሎችም አጫጭር ታሪኮች (በመክብብ አበበ) እና ልብስ ሰፊውና አራቱ አይጦች (በበኃይሉ ገብረ እግዚአብሔር) ደግሞ በልጆች መጽሐፍ ዘርፍ የታጩ ናቸው፡፡

ማታ ማታና ሌሎች ትረካዎች (ከሕይወት እምሻው)፣ የምወድህ (ከሊዲያ ተስፋዬ)፣ አልፎ ያላለፈና ሌሎችም (ከሱለይ አዳም) በአጭር ልቦለድ የታጩ መሆናቸውን አዘጋጁ ተናግረዋል፡፡

በግጥም መጽሐፍት ዘርፍ ደግሞ እግዜርና ጥበቡ (በዘካሪያስ ገብረ ሚካኤል)፣ ኮብላይ ዘመን (በተሾመ ብርሃኑ)፣ የነቢያት ጉባዔ (በባለቅኔ ሙሉጌታ ተሰፋዬ)  የሚወዳደሩ ናቸው።

 የባህር ኃይሉ ራስወርቅ (በፒቲ ኦፊሰር ራስወርቅ መንገሻ) ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር) በአንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሕይወቴ (በደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ)፣ ዳኛው ማነው (ታደለች ኃይለ ሚካኤል)፣ ከሰንጋ ተራ እስከ አምስተርዳም (በመላኩ ተገኝ) የሚወዳደሩ ይሆናል በግለ ታሪክ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡ ናቸው፡፡

በጥናትና ምርምር

አንድሮሜዳ – የጥንት ኢትዮጵያውያን የሕዋ ሥልጣኔ ከዘመናዊው ህዋ አንፃር (ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) እና ጌትነት ፈለቀ (ዶ/ር))፣ ኢትዮጵያዊው ሱራፌ (የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የሕይወት ታሪክና አስተዋጽኦ (በዲያቆን ዳናኤል ክብረት)፣ ነቅዐ መጻሕፍት  ከ600 በላይ በግዕዝ የተጻፉ የኢትዮጵያ መጽሐፍት ዝርዝር ከማብራሪያ ጋር (ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ) በጥናትና ምርምር ዘርፍ የታጩ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የሐበሻ ከዋክብት ቅጽ አንድና ሁለት (በሼክ ሙሐመድ ኢብራሂም)፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ (1921-1983) በአስፋው አየልኝ (ኮሎኔል) በግለ ታሪክ ከቀረቡ ዕጩዎች ናቸው፡፡

በሁሉም ዘርፎች አንደኛ የሚወጡ መጽሐፍት የዓመቱ ምርጥ መጽሐፍ ሽልማት አሸናፊዎች ይሆናሉ።

ይህንንም መለየት ሒደት ከአንባቢያን የሚሰጥ ድምፅ 20 በመቶ ዋጋ የሚኖረው ሲሆን፣ ዳኖች በዳግም ግምገማ የሚሰጡት ውጤት 80 በመቶ የሚይዝ ይሆናል፡፡ በመሆኑም አንባቢያን ማሸነፍ አለበት የሚሉትን መጽሐፍት በሆሔ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት የፌስ ቡክ ገጽ በመግባት መምረጥ እንደሚችሉ አዘጋጁ ገልጸዋል፡፡

የሆሔ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በንባብ ለሕይወት ዓውደ ርዕይ እንደሚሳተፉ፣ ለዕጩነት የቀረቡ መጽሐፍት ላይ ሙያዊ ሂስ እንደሚሰጥባቸው አቶ ኤፍሬም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...