Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ከታክስ በኋላ 50 ቢሊዮን ብር ማትረፋቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ባለፉት አራት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት አስመልክቶ እንዳስታወቀው፣ እ.ኤ.አ. በ2019 የባንኮቹ ካፒታል 98 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ የካፒታል መጠናቸው በየዓመቱ 25 በመቶ ዕድገት በማሳየቱ፣ በ2014 ሒሳብ ዓመት ማጠናቀቂያ የካፒታል መጠናቸው 199.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብሏል፡፡

ከትርፋማነት አኳያም ባንኮች ከፍተኛ ዕድገት እያሳዩ መሆናቸውን፣ በ2011 የሒሳብ ዓመት 22 ቢሊዮን ብር የነበረው የተጣራ ትርፋቸው በ2014 ሒሳብ ዓመት ማጠናቀቂያ 49.9 (50) ቢሊዮን ብር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር አያሌው ገልጸዋል፡፡

በ2011 የሒሳብ ዓመት 18 የነበረው የባንኮች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 30 መድረሱንም አቶ ፍሬዘር ጠቁመዋል፡፡ 

ብሔራዊ ባንክ

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች