Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየፌዴሬሽኑ ቀጣይ ምርጫና የሊጉ አክሲዮን ማኅበር መግለጫ

  የፌዴሬሽኑ ቀጣይ ምርጫና የሊጉ አክሲዮን ማኅበር መግለጫ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ  ፌዴሬሽን በቅርቡ ያከናውነዋል ተብሎ በሚጠበቀው የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ጋር በተገናኘ፣ ከወዲሁ እየተሰማ ያለው አለመግባባትና ውዝግብ ሥጋት ፈጥሮብኛል አለ፡፡ ገለልተኛና ፍትሐዊ ምርጫ ሊደረግ እንደሚገባ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳስቧል፡፡

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ፣ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ለሚደረገው የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ሦስት፣ ሦስት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከዚሁ አስመራጭ ኮሚቴና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አሰያየም ጋር በተገናኘ፣ አባላቱ የገለልተኝነት ጥያቄ እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡

  ከተመሠረተ አራተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር፣ ከፌዴሬሽኑ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫን ተከትሎ፣ በተለይ በምርጫ አስፈጻሚነት የተሰየሙት አባላት ምርጫውን በገለልተኝነት ያስፈጽማሉ ብሎ እንደማያምን ማከሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሥጋቱን ይፋ አድርጓል፡፡

  የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሊቀመንበር መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣ ከገለልተኝነት ጋር በተያያዘ በመግለጫው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፣ አክሲዮን ማኅበሩ ምርጫውን ተከትሎ በማይመለከተው ጉዳይ መግለጫ የሚሰጥ ከሆነ፣ ፈዴሬሽኑ በሕግ የሚጠየቅ ስለመሆኑ ጭምር የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡

  ምርጫው ገለልተኛና ፍትሐዊ እንዲሆን መጠየቅ በሕግ የሚያስጠይቅ ከሆነ ‹‹ልጠየቅ›› ያሉት የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ፣ በፌዴሬሽኑ የነበሩ ከአሠራርና ግልፀኝነት ጋር በተገናኘ፣ 95 ሚሊዮን ብር ግዥ የተፈጸመበት የፌዴሬሽኑ ሕንፃ የባለቤትነት ሒደቱ ሳይጠናቀቅ ሙሉ ክፍያ መከፈሉ፣ በዚህም ተቋሙ የባለቤትነት ስም ለማዞር ፌዴሬሽኑ ተጨማሪ ስምንት ሚሊዮን ብር ክፍያ መክፈል የሚጠበቅበት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

  ሌላው ስለ አስመራጭ ኮሚቴውና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው የገለልተኝነት ጉዳይን በተመለከተ የቦርድ ሰብሳቢው፣ ‹‹አስመራጭ ኮሚቴውን በሰብሳቢነት እንዲመሩ የተሰየሙት አቶ ኃይሉ ሞላ የፌደሬሽኑ የሕግ አማካሪ የነበሩ ናቸው፡፡ ምክትላቸው አቶ መንግሥቱ መሐሩ ደግሞ የፌዴሬሽኑ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ ከአስመራጭ ኮሚቴው ጎን ለጎን የተሰየመው ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውስጥ አንደኛው የመንግሥት ሹመኛ ሲሆኑ፣ በምርጫ ሕጉ መሠረት ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ከሚሾሙት መካከል አንደኛው የሕግ ባለሙያ መሆን ይኖርበታል ይላል፣ ነገር ግን ከአባላቱ የሕግ ባለሙያ የለም፤›› ብለዋል፡፡

  አክሲዮን ማኅበሩ በመግለጫው እነዚህና ሌሎችም ከምርጫው ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ከወዲሁ ሊስተካከሉ እንደሚገባ ጠይቋል፡፡ ሁኔታው እርምት ሳይደረግበት ችግሩ ተፈጥሮ ውድድሮች የማይከናወኑ ከሆነ ግን፣ ያለው አክሲዮን ማኅበሩ፣ ሊጉ ከዲኤስ ቲቪ ጋር የረዥም ዓመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ያለው በመሆኑና ጉዳይ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ፊት የሚያስቀርብ ከመሆኑ ባሻገር፣ የሚያስከትለው ኪሳራም ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...

  መኖሪያ ሸጦ መዞሪያ!

  እነሆ ከመካኒሳ ወደ ጀሞ ልንጓዝ ነው። ቀና ሲሉት እየጎበጠ...

  በምግብ ራሳችንን የመቻል ፈተና

  በጋሹ ሃብቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በምግብ ራሳችንን መቻል እጅግ በጣም የተወሳሰበ...