Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበኮሎምቢያ ካሊ በወጣት አትሌቶች በሜዳሊያ የተንበሸበሸው ብሔራዊ ቡድን ዓርብ አቀባበል ይደረግለታል

በኮሎምቢያ ካሊ በወጣት አትሌቶች በሜዳሊያ የተንበሸበሸው ብሔራዊ ቡድን ዓርብ አቀባበል ይደረግለታል

ቀን:

በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የዓለም ወጣቶች አትሌቲከክስ ሻምፒዮና ላይ በ19 አትሌቶች የተወከለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ከምጊዜውም የላቀ ውጤት አስመዝግቦ ሻምፒዮናውን አጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በተለይ ለኬንያውያን የባህል ጨዋታ ተደርጎ ሲነገርላቸው በነበሩ የውድድር ዓይነቶች ላይ ጥንካሬያቸውን ያስመሰከሩበት የውድድር መድረክ ሆኖ አልፏል፡፡

በካሊ ከተማ ከሐምሌ 25 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን፣ በሻምፒዮናው የመጨረሻዎቹ ቀናት በአንድ ምሽት ብቻ አራት የወርቅና ሦስት የብር ሜዳሊያ በማስመዝገብ፣ በአጠቃላይ ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብርና አንድ የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን ሰብስቦ፣ ከዓለም ከአሜሪካና ጃማይካ ቀጥሎ ሦስተኛ፣ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡

በ5,000 ሜትር የመጀመርያውን ሜዳሊያ በአሰላ ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል ሥልጠናውን በተከታተለው፣ አዲሱ ይሁኔ አማካይነት አንድ ብሎ የጀመረው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን፣ በተመሳሳይ ሴቶች በመዲና ኢሳ አማካይነት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሳምንት በፊት በአሜሪካ ኦሪገን ከተማ በዩጂን ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን፣ ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን በነበረው ተሳትፎ አራት የወርቅ፣ አራት የብርና ሁለት የነሐስ በድምሩ አሥር ሜዳሊያዎችን በመስመዝገብ ከዓለም ሁለተኛ በመሆን በሻምፒዮናው የላቀውን ውጤት አስመዝግቦ መመለሱ ይታወሳል፡፡

በኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት ሳይደበዝዝ፣ በኮሎምቢያ ካሊ በወጣቶቹ ከምግዜውም የተሻለ ውጤት መመዝገቡ፣ ኢትዮጵያ በቀጣይ በስፖርቱ የበለጠ ተጠቃሚ መሆን የምትችልበትና የማይነጥፍ ሀብት ባለቤት እንደሚያደርጋት ጭምር እየተነገረ ይገኛል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት የኬንያውያን አትሌቶች የባህል ስፖርት እንደሆነ ተደርጎ ሲነገርለት የነበረው፣ 3,000 ሜትር መሰናክልና 3,000 ሜትር ቀጥታ እንዲሁም በአጭርና መካከለኛ ርቀት የውድድር ዓይነቶች በካሊ ከተማ በነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌትቲክስ ሻምፒዮና፣ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት መጠናቀቁ፣ በወርልድ አትሌቲክስ ሳይቀር መነጋገሪያ ሆኖ አልፏል፡፡

በወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል የድሉ ባለቤት ርቀቱን 8፡37.92  ያጠናቀቀው ሳሙኤል ድጉማና እሱን ተከትሎ 8፡39.11 ያጠናቀቀው ሳሙኤል ፍሬው የወርቅና የብር ሜዳሊያ አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ሌላው በ3,000 ሜትር ቀጥታ ሩጫ መልክነህ ኢዚዝ ርቀቱን 7፡44.06 አጠናቆ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነበት መድረክም ነበር፡፡

በርቀቱ ባልተለደመ መልኩ ውጤታማ ከሆኑት አትሌቶች መካከል በሴቶች በ1,500 ሜትር በአስደናቂ ብቃት የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው ብርቄ ኃየሎም ስትሆን፣ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ጊዜ 4፡04.27 ነበር፡፡ በ800 ሜትር ወንዶች ኤርምያስ ግርማ ርቀቱን 1፡47.36 በመግባት ለአገሩና ለራሱ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበ አትሌት ሆኗል፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ በተካሄደው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ኢትዮጵያ በአሥር የውድድር ተግባራት ብቻ ያስመዘገበችው ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብርና አንድ የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎች፣ ከዓለም አገሮች ከአሜሪካና ጃማይካ በመቀጠል ያስመዘገበችው ውጤት፣ በሻምፒዮናው እስካሁን ከተደረጉ ከ20 ዓመት በታች የዓለም የውድድር መድረክ፣ በውጤት ደረጃ ከፍተኛው ነው፡፡ ቡድኑ ዓርብ ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ አገሩ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...