Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ዕውቅና ቤት ለቤት ልብስ ለሚያጥቡ ሴቶች

ትኩስ ፅሁፎች

ሴቶች በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን፣ መላው ቤተሰብም ሙሉ የዕለት ተዕለት ኑሮው በሴቶች ላይ የተደገፈ ነው፡፡ ሴቶች የእያንዳንዱን ሰው ፍላጎት ከማሟላታቸው ባሻገር እናት፣ ሚስት፣ የቤት ውስጥ ሥራዎችንና ኃላፊነቶች አከናዋኝ፣ ምግብ አብሳይ፣ አስተማሪ፣ ጓደኛና የመላ ቤተሰቡ ተንከባካቢ በመሆን በርካታ ሚናዎችን በአንድ ጊዜ ይጫወታሉ፡፡ በሌላ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶችም ቤታቸውንና ቤተሰባቸውን ከሥራ ኃላፊነታቸው ጋር ማመጣጠን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሴቶች በጣም ከባድ ሕይወትን በሁሉም መስክ የሚመሩ ቢሆንም፣ ስለልፋታቸው ምንም ዓይነት ምሥጋና ወይም ዕውቅና አይሰጣቸውም፡፡

የሚያስገርም ችሎታ ያላቸውና ብዙ ሥራዎችን የሚሠሩ፣ ነገር ግን ከሚኖሩበት ማኅበረሰብ ዕውቅና የተነፈጉም አዕላፍ ሴቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በየቤቱ እየተዘዋወሩ ልብስ የሚያጥቡ ሴቶች ይገኙበታል፡፡

ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ፣ በከተማ ለሚገኙና እየተዘዋወሩ ልብስ ለሚያጥቡ ሴቶች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

ዕውቅና ቤት ለቤት ልብስ ለሚያጥቡ ሴቶች | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር  

(ፎቶ በመስፍን ሰለሞን)

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች