የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንደር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ፣ ሁለቱም በጋራ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተወሰደ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፓንደር አገራቸው ደቡብ አፍሪካ በዩክሬን፣ በቻይና፣ በእስራኤልና በፍልስጥኤም ጉዳዮች ከአሜሪካ ጋር በግልጽ የሚታይ ልዩነት እንዳላትም አስታውቀዋል፡፡ ‹‹በአውሮፓና በሌላ ሥፍራ ከሚገኙ የተወሰኑ አጋሮቻችን ጋር ስንነጋገር የአዛዥነትና የተቆጣጣሪነት ስሜት እንዳለ እንረዳለን፡፡ ከዚያም አልፎ ተርፎ ለእኛ አፍሪካውያን ስለዴሞክራሲ ትምህርት ሊሰጡን የሚፈልጉም አሉ፡፡ ከዚህና ከዚያኛው እንደንመርጥም ይነገረናል…›› ሲሉ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች የሚያደርጉትን ጉብኝት በደቡብ አፍሪካ ሲጀምሩ ነው፣ ይህንን ዓይነቱ ጠንከር ያለ ንግግር ከደቡብ አፍሪካዋ ወይዘሮ የጠበቃቸው፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ናቸው፡፡