Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምቻይናና ታይዋን የተወዛገቡበት የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት

ቻይናና ታይዋን የተወዛገቡበት የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት

ቀን:

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ለመጎብኘት ማቀዳቸው ከተሰማ ጀምሮ ቻይና ተቃውሞዋን ስታሰማ ከርማለች፡፡ የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እንደአንድ ግዛቷ በምትቆጥራት ታይዋን ላይ ያላትን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሚያበላሽ እንዲሁም ጣልቃ ገብነት ነው ስትልም አፈ ጉባዔዋ ታይዋንን እንዳይረግጡ፣ ከረገጡ ደግሞ መዘዙ ከባድ እንደሚሆን ስታስጠነቅቅም ነበር፡፡ ሆኖም ከወደ አሜሪካ በኩል የቻይና ዛቻና ማስጠንቀቂያ ጆሮ ሳይሰጠው ቀርቶ፣ ፔሎሲ ለ19 ሰዓታት ያህል በታይዋን የቆዩት ባለፈው ሳምንት ነው፡፡

ከታይዋን ፕሬዚዳንት ስያንግ ዊን ጋር ውይይት ያደረጉት ፔሎሲ፣ የታይዋን ሕግ አውጭዎችን እንዲሁም የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ወትዋቾችንም ጎብኝተዋል፡፡ ይህ በሩሲያና በዩክሬን መካከል ከአምስት ወራት በፊት የተቀሰቀሰው ጦርነት ሳያበቃ፣ በቻይናና በታይዋን መካከል አዲስ ጦርነት እንዲጀመር ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚሉ ትንበያዎች ከየአቅጣጫው እንዲሰሙ አድርጓል፡፡

የዩክሬንና የሩሲያ ጦርነት በዓለም የምግብና የነዳጅ ዋጋ እንዲጋሽብ ከማድረጉ ባለፈ የዓለምን ፖለቲካ አናግቶታል፡፡ በዋናነት አሜሪካና አውሮፓ በአንድ ሆነው ለዩክሬን፣ ቻይና፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ኢራን፣ ቤላሩስ ለሩሲያ ወግነው የአፍሪካ አገሮች ደግሞ ደግሞ ከዳር ሆነው ቱርክ እያሸማገለች የሚከታተሉት ይህ ጦርነት ሳያባራ በቻይናና ታይዋን መካከል የነገሠው የጦርነት ጉምጉምታና ወታደራዊ ልምምድ ለዓለም ሌላ ሥጋት ይዞ መጥቷል፡፡

ቻይናና ታይዋን የተወዛገቡበት የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ናንሲ ፔሎሲ ከግራ ከታይዋን ፕሬዚዳንት ሳይንግ ዊን ጋር

የናንሲ ፔሎሲን ጉብኝት ያወገዙት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ቶ፣ ‹‹ጉብኝት አሜሪካ በታይዋንና በቀጣናው መረጋጋትና ሰላም እንዳይፈጠር የምታደርገውን ሥራ ያሳያል ትልቅ አጥፊ›› ናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለናንሲ ፔሎሲ ጉብኝት ምላሽ የቻይናን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ማንኛውንም ዕርምጃ ትወስዳለች፣ ማንኛውም ክስተት መነሻውም ከአሜሪካና ከታይዋን የነፃነት አቀንቃኞች ኃይል ነው ብለዋል፡፡

ጉብኝቱን ተከትሎ በታይዋን አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ የጀመረችው ቻይና፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የምግብ ዓይነቶች ከታይዋን ወደቻይና እንዳይገቡም አግዳለች፡፡

ከወደቻይና የተሰነዘረ ነው የተባለ የሳይበር ጥቃት የታይዋን የመንግሥት ድረገጾች፣ አንዳንድ የታይዋን መደብሮች እንዲሁም የመንግሥት ተቋማትን ለተወሰነ ጊዜ አቋርጦት እንደነበር ካውንስል ኦን ፍሪን ሪሌሽንስ በድረገጹ አስፍሯል፡፡

ቻይና የፔሎሲን መምጣት ተከትሎ በታይዋን አቅራቢያ የጀመረችው ወታደራዊ ልምምድ በአጭር ጊዜ ያበቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ቻይና አዲስ ልምምድ መጀመሯንም አስተውቃለች፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበውም፣ ቻይና ተጨማሪ ወታደራዊ ልምምዷን በታይዋን አካባቢ በባህርና በአየር ላይ እያካሄደች ነው፡፡ የታይዋን መከላከያ ላይ ጫና ለማሳደርም እየሠራች ትገኛለች፡፡

ቻይና አዲስ የጀመረችው ወታደራዊ ልምምድ መቼ እንደሚያበቃና ትክክለኛ ሥፍራው የማይታወቅ ቢሆንም፣ ቻይና ወታደራዊ ልምምድ በምታደርግባቸው ስድስት ዞኖች በረራ አግዳ የነበረችው ታይዋን አሁን ላይ የበረራ ዕገዳውን አላልታለች፡፡

ቻይና 11 ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ባለስቲክ ሚሳየሎች በመጀመሪያዎቹ አራት የወታደራዊ ልምምድ ቀናት ያስወነጨፈች ሲሆን፣ የቻይና የጦር መርከቦች ተዋጊ ጀቶችና ድሮኖች በልምምዱ ተሳታፊ ነበሩ፡፡

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ የቻይና 66 ተዋጊ ጀቶች 14 የጦር መርከቦች የባህርና የአየር ልምምድ ማድረጋቸው ማወቁን ተናግሯል፡፡

አሜሪካ ከ25 ዓመታት በኋላ ከፍተኛ ባለሥልጣኗን ወደ ታይዋን መላኳ በቻይናና በታይዋን መካከል ቀድሞ የነበረውን ውጥረት ያባባሰው ሲሆን፣ የቻይናም ይህንን ‹‹የአንድ ቻይና ፖሊሲ››ን መጣስ አድርጋ ትቆጥረዋለች፡፡

በፖሊሲው መሠረት ቻይና ሉዓላዊነት አገር ስትሆን ይህም ታይዋንን ያጠቃልላል፡፡ አሜሪካም ሆነች ሌሎች አገሮች ይህንን ፖሊሲ ይቀበሉታል፡፡ ግንኙነታቸውንም የሚያደርጉት ከቻይና ጋር እንጂ ከታይዋን አይደለም፡፡

ቻይና ይህ ሁሌም ተጠብቆ እንዲቆይ የምትፈልግ ቢሆንም፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከሁለት አሥርት በኋላ የታይዋን ምድርን ረግጠዋል፡፡ ታይዋን ራሷን መከላከል አለባት በማለትም መሣሪያ ከወደአሜሪካ ይቀርባል፡፡ ይህ በቻይና በኩል ተቀባይነት የለውም፡፡ በመሆኑም ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት አሻክሯል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1972 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን በቻይናና አሜሪካ መካከል የፈጠሩት ግንኙነት ሁለቱ አገሮች በኢኮኖሚ እንዲደጋገፉ አብረው እንዲሠሩ በር ከፍቶ ለዓመታት የዘለቀ ቢሆንም፣ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ግንኙነታቸው እየተበረዘ መጥቷል፡፡ የቃላት ጦርነቱም አይሏል፡፡

የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ሰላማዊ ነው በማለት በአሜሪካ በኩል ቢነገርም፣ ቻይና “ፀብ አጫሪነት ነው” ስትል ነቅፋዋለች፡፡ ለምላሹም ታይዋንንም ሆነ ምዕራባውያንን ያስጨነቀ የጦር ልምምድ ጀምራለች፡፡ በኒክሰን ዘመን የተገነባው የአሜሪካና የቻይና ግንኙነትም በናንሲ ፔሎሲ ጉብኝት እንደዋዛ መናዱን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...